የውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ፣ኒው ሆራይዘን ፎር አፍሪካ፣ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበርና አፍሪካን ኤግል መልቲሚዲያ በጋራ የሚዘጋጁት ይህ ፕሮግራም “የጥቁር ሉአላዊነት ” በሚል መሪ ቃል የሚዘከር ይሆናል።
ከየካቲት 1 ጀምሮ ለተከታታይ 28 ቀናት የጥቁሮች ታሪክ በሚዘከርበት ወር ለጥቁር ህዝቦችና ለሌሎችም አርአያ መሆን የቻሉ ጥቁር 28 ሴቶች ታሪክ ይዘከራል ሲሉ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
ሚሼል ኦባማ ፣ኦፕራ ዊንፍሬና ኢትዮጵያ ሀብተማርያምን የመሳሰሉ የጥቁር ልህቀትን ለአለም ያሳዩ ከሚዘከሩት ሴቶች መካከል ናቸው።
በህክምና በትምህርት በሙዚቃ እና በተለያዩ የስራ ዘርፎች የላቀ ታሪክ ያላቸው ሴቶችም በዝክረ ታሪክ ውስጥ ተካተዋል።

ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ከ25 በላይ ጥቁር አሜሪካውያንም ፕሮፌሰሮች ፣ሳይንቲስቶች፣ ዶክተሮችና ሌሎች ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ናቸው ።
በፓንአፍሪካኒዚም፣በጥቁር ተጽዕኖ ፈጣሪነት ፣በአፍሪካዊያን ጥምረት ላይ ከመላው አለም ከሚገኙ ጥቁር ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር ከሚደረግ የዙም ውይይት ባሻገር
፣በኢትዮጵያ ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት አሻራ የሆኑ መዳረሻዎች ይጎበኛሉ።
ወሩን ለመዘከር ኢትዮጵያ መመረጧ ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ያደረገችውን ተጋድሎ ምክንያት በማድረግ ነው ።
ይህ ፕሮግራም በየአመቱ ቀጣይነት እንዲኖረውና ለዲፕሎማሲውም ሆነ ለአገር ገጽታ ግንባታ ጠቃሚ በሆነ መልኩ እንደሚሰራ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
ጥቁር አፍሪካ አሜሪካውያን የየካቲት ወርን የጥቁር ህዝብ የታሪክ ወር በሚል ሰይመው መዘከር ከጀመሩ 50 አመት በላይ እንደሆናቸው መረጃዎች ያሳያሉ።