የገቢዎች ሚኒስቴር አየር መንገድ ለሰራተኞቹ በሚሰጠው ነፃ ትኬት የንግድ እቃዎችን በብዛት እየመጡ ሰለሆነ ማንኛውም በነፃ ትኬት ውጭ የሚሄድ የአየር መንገድ ሰራተኛ ይዞ በሚመጣው እቃ ላይ ሶስት እጥፍ ቀረጥ እጥላለው ማለቱ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
ገቢዎች በዚህ አሰራሩ ለሌላውም መንገደኛ እንደሚያደርገው በቁጥር 60 በአይነት አራት ከቀረጥ ነፃ የሚፈቅደውን አልባሳት ለአየር መንገዱ ሰራተኞች ከልክሎ አንድም ልብስ ከውጭ ቢያመጡ እንደሚቀርጥ አስታውቋል።
ሚኔስቴሩ ከሳምንት በፊት ዱባይ በተጓዙ የአየር መንገዱ ሰራተኞች ላይ ተግባራዊ አርጎ ከዛም በተቃውሞ የጣለውን የሶስት እጥፍ ቀረጥ ያነሳ ቢሆንም አሰራሩ ሙሉ ለሙሉ መልሶ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ይሄ አዲስ አሰራር በሁለት ሻንጣ ልብስ ላይ እሰከ መቶ ሺ ብር ድረስ ሊቀርጠን ይችላል በማለት የአየር መንገዱ ሰራተኞች ተቃውሞ አሰምተዋል ።
በስልክ ለፊደል ፓስት ቅሬታዋን የገለፀቸው ሄለን የተባለች የአየር መንገዱ ሰራተኛ እንዳለችው ” እኛ ነፃ ትኬት አገኘን እንጂ ውጭ ስንሄድ ልብስ በነፃ አናመጣም ።እንድ መንገደኛ ከቀረጥ ነፃ የሚፈቀድ ነገረ ሊፈቀደልን ይገባል ።ከዛ በላይ በሆነ ነገር ደግሞ እንደመንገደኛው ልንቀረጥ ይገባል።አዲሱ አሰራር አድሏዊ ነው።የአየር መንገድ ሰራተኛ ለሀገሪቷ ትልቅ ገቢ እያስገባ ገና ለገና በነፃ ትኬት ሄደሀልና አንድም ልብስ ብታመጣ ትቀረጣለህ ማለት ለእኛ ክብር አለመስጠት ነው ” ብላለች ።
የአየር መንገዱ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ለሚኒስቴር መሰርያቤቱ በፃፈው ደብዳቤ በአመት ከሁለት ጉዞ በላይ በነፃ ትኬት ውጭ ደርሰው የሚመጡትን የአየር መንገዱን ሰራተኞች እንደ ነጋዴ ማየት ተገቢ አይደለም እንደከዚ በፊቱ መንገደኞች በሚቀረጡበት አይን ሊታዩ ይገባል በማለት አዲሱ መመርየ እንዲቀር ጠይቋል ።
We would like our esteemed company along with Ethiopian customs airport branch to take it into consideration
Yehe adiloawi aserar higin yalteketele fitsum yehager zega keandu meleyayet lay yatekore new ,kefitegna e fitawi aserar yemetayibachew airport customs westachew letara behigi ledagu yegebal !