ፊደል ፓስት ከሆቴል አማካሪዎች ባገኘው መረጃ በ33 ኛው የአፍሪካ መሪዎች ሰብሰባ ባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴሎች አልጋቸው ከ90 ፐርሰንት በላይ ተይዞ የነበረ ሲሆን ባለ ሶስት ኮከብ ሆቴሎች ደግሞ ከአስር የመኝታ ክፍሎቻቸው ሰባቱ ተይዘው ነበር ።
በዋጋም አንፃር ሲታይም ሆቴሎቹ ከመደበኛ ዋጋቸው ከ50 አስከ 80 ዶላር ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን በስብሰባው ቀናቶች የአንድ አዳር ከ150 ዶላር አስከ 300 ዶላር ድረስ ይከፈል አነደ ነበር የሆቴል አማካሪዎቹ ተናግረዋል ።
ረዲሰን ብሉ ፣ራማዳ፣ጎልደን ቱሊፕ፣ ሀያት ሪጀንሲ ፣ማርዮት ፣ቤስት፣ ዌስተርን ፣ሸራተን አዲስ ፣ኢንተር ኮንትኔንታል አዲስ ፣ኢሊሊ ፣ሂልተን ሆቴሎች ጥሩ የተባለ ገቢ በስብሰባው አስገብተዋል።
በ33 ኛው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ከ2,500 በላይ እንግዶች አዲስ አበባ መጥተው ነበር ።