ከግል የጡረታ አበል ተከፋዮች ውስጥ 89,000 ብር በወር የሚከፈለው ግለሰብ አለ



የቀድሞ የናሽናል ኦይል ሰራተኛ የነበረ ግለሰብ በኢትዮጵያ ከግል ጡረተኛ ተከፋዮች ውስጥ 89,000 ብር በወር የጡረታ አበል በማግኘት የመጀመረያ ደረጃ ሲይዝ ሌላ በዶክተርነት ማእረግ ያለች ሴት 80,000 ብር እንደሚከፈላት ፊደል ፓስት ያገኘው መረጃ ያሳያል ።66,000 ብር ደግሞ በሶስተኛ ደረጃ በወር የሚከፈል የጡረታ አበል ሆኖ ተመዝግቧል።

በአሁኑ ሰአት የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማኀበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ትንሹ ወርሀዊ የአበል ክፍያ 1,258 ብር ነው።

የዕርጅና ጡረታ መጠን ሰራተኛው ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ያገኘው የነበረው አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ 30% ሆኖ በዚህ ላይም ዋስትና ያለው ሰራተኛ ከ10 ዓመት በላይ ለፈፀመው ለእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ 1.25% (ወታደር ያልሆነ) ወይም 1.65% (ወታደር) በመደመር ይታሰባል፡፡ የመጀመሪያ ጡረታ አበል እንደ እርጅና ጡረታ አበል በተመሳሳይ ሊሰለፍ አንድ ሰራተኛ በ60 አመት እድሜው ለእርጅና ጡረታ ብቁ የሚያደርጉትን ሁኔታዎች የማያሟላ ከሆነ የሰራተኛው መነሻ ወርሃዊ ደመወዝ ጡረታ ከመውጣቱ አንድ ወር በፊት የነበረው ደመወዙ በአገልግሎት ዘመኑ እና መዋጮው ይከፈለዋል።
የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በ2003 የተመሰረተ ነው። ተቋሙ ከዚህ ቀደም ከ1953 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት አባላት የጡረታ ሽፋን ሲሰጥ ነበር። ነገር ግን የግል ድርጅት ሠራተኞች የማሕበራዊ ዋስትና ወይም የጡረታ ሽፋን አልነበራቸውም። የግል ድርጅት ሠራተኞች በተለይ በመደበኛው ዘርፍ ያሉ ደመወዝ እየተከፈላቸው ተቀጥረው የሚያገለግሉ የማሕበራዊ ዋስትና ሽፋን ማግኘት አለባቸው በሚል ምክንያት ነው የተቋቋመው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *