የኮሮና ቫይረስ ገበያውን የቀነሰበት ኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ሊቀንስ እንደሚችል ጠቁሟል



የኮሮና ቫይረስ የጠቅላላ የጉዞ በረራውን ከ20 ፐርሰንት በላይ የቀነሰበት 16,000 ገደማ ሰራተኛ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰራተኞቹ ከሳምንት በፊት በላከው የኤሜይል መልእክት በአየር መንገዱ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቢሮዎችን አሁን ካለው ገበያ አንፃር አይተው አላስፈላጊ የተባሉ ቢሮዎችን እና ሰራተኞችን እንዲቀንሱ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ሰራተኞቹ ያልተጠቀሙበት የቫኬሽን ጉዞ ካለ ቶሎ እንዲጠቀሙበትም አሳስቧል።

በተጨማሪም ከአየር መንገዱ የሚሰሩ ኤርፓርቶች፣ምግብና መጠጥ አቅራቢዎች፣ ሆቴሎች ጠበቆች፣የነዳጅ አቅራቢዎችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች የዋጋ ቅናሽ እና አንዲያደርጉና ለጊዜው ውል እንዲያቋርጡ ጉዳዩን ለሚመሩት የአየር መንገድ ክፍል ሀላፊዎች አሳስቧል።
አየር መንገዱ የገበያ መቀነሱን ወጪውን ለማጣጣም በሊዝ የተከራያቸውን ፕሌኖች በቅናሽ ዋጋ ለመከራየት አልያም ለጊዜው ለመተው የውል ድርድር እያደረገ መሆኑንም ጠቁማል።


አየር መንገዱ እቃ የሚየጓጉዝባቸው አስር B-777F እውሮፕላኖች እያንዳንዳቸው በቀን 11 ሰአት በአሁን ሰአት አንደሚበሩ ገልፇ አለም ላይ በቅርቡ ተስፈንጥሮ ያደገውን የአየር ላይ የእቃ ጉዞ እድልን ተጠቅሞ እያንዳንዱ እውሮፕላን በቀን 17 ሰአት ሊበር እንደሚገባም አሳስቧል ።
በቀን ስድስት አየበረሩ ያሉት ሁለቱ B-738F የእቃ ሟጓጓዣ አውሮፕላኖች እያንዳንዳቸው 13 ሰአት በቀን መብረር ይጠበቅባችዋልም ብሏል።
ፊደል ፖሰት ባገኘው መረጃ መሰረት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአየር መንገዱ የቻይና በረራ ቀንሶ በየቀኑ ይኬድ የነበረው የኢትዮጵያ የቻይና ጉዞ በሳምንት ሶስቴ ሆኗል። ይሄም የአየር መንገዱን ገቢ ላይ አሉታዊ ጫና አሳድሯል።
ነገር ግን በቻይና በዚህ ሳምንት የታየውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመጠኑ መቀነስን ተከትሎ አየር መንገዱ ባለፉት ሶስት ቀናት በመጠኑ የተሻለ ያለ ተሳፋሪዎችን ቁጥር ማስተናገዱን ምንጮች ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *