የሌጎስ ፓሊስ ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በከተማዋ የሚገኝ የመቃብር ስፍራን ቆፍረው ከሬሳ ላይ የሰው ቅል እያወጡ ለቅጠላ ቅጠል ቀማሚ ሲሸጡ የነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎችን መያዙን አስታውቋል።
የፖሊስ ቢሮው ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ባላ ኤልካና እንዳሉት ከተጠርጣሪዎች መሀከል አንዱ መቃብር ቆፋሪ ሲሆን ከመቃብር ላይ የሰው ቅል አያዋጣ ይሸጥ እንደነበር ምርመራ ላይ አምኗል ብለዋል።
ኢድዋላ ቲያንጂ የተባለው ተጠርጣሪ በሌጎስ የቀለበት መንገድ ላይ ባለ የባስ መቆሚያ ጋር ቡኒ ፌስታል ይዞ ሲጓዝ እንደነበረና ፓሊስ ሲፈትሸውም በያዘው ፌስታል ውስጥ ያለው የሞተ ሰው የራስ ቅል መሆኑን ተናግረዋል
ሌላው ተጠርጣሪ ኦላዋሌ ሻድሙሉ የተባለው ቀማሚ የራስ ቅሉን በአስር ሺ ናይራ ሊገዛ እንደነበር ተናግሯል።
ቀማሚው የራስ ቅሉንም በመፍጨትና ከሌላ ቅጠል ጋር በመቀላቀል እሱ ጋር ለሚመጡ ሰዎች ደስታን እንዲያገኙ ለማድረግ እንደ መድሀኒት አንዲወስዱት ያደርግ እንደነበር የተነገረ ሲሆን ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ ለፍርድ እንደሚቀርቡም ተገልፇል።