ፊደል ፓስት ከኢትዮጰያ አየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ ሰራተኞች ማህበር አባላት ባገኘው መረጃ አየር መንገዱ የሰራተኛ ማህበሩ በነፃ እንዳይንቀሳቀስ የተለያዪ ጫና አያደረሰ በመሆኑ ይሄንን ነገር ሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይን ጨምሮ ለተለያዩ የመንግስት መስርያ ቤቶች ብናሳውቅም ምላሽ ስላልተሰጠን በመጪው ስድስት ሳምንታት ውስጥ መልስ ካላገኘን ቅሬታችንን በአንድነት በመሰባሰብ በአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት እየተዘጋጁ እንደሆነ ገልፀዋል:
ጫናዎችን በተለመከተፊደል ፓስት ያነጋገራቸው ሰራተኞች ሰራተኛውን በማስፈራራት አዲሱ ማህበር እንዳይቀንሳቀስ የሚደረግ ህገወጥ ድርጊት በመበራከቱ ማህበሩ 5,000 የሚጠጉ አባላት ቢኖሩትም በነፃነት መስራት አልቻልንም ብለዋል።