የኮሮና ተፅእኖ ኢትዮጵያ ያሉ ሆቴሎችን ሰራተኛ ቁጥር በግማሽ ሊያስቀንስ ይችላል ተባለ


ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የቱሪስት መጠን መቀነስ ፣የኢኮኖሚ መቀዛቀዝና ከ30 በላይ የአየር መንገድ አለም አቀፍ በረራዎች መሰረዝ ተከትሎ መንገደኞች መቀነስ በኢትዮጵያ ያሉትን አብዛኞቹ ሆቴሎች ከአስር አልጋ ሶስት ወይም አራት አልጋቸው አየተያዘ መሆኑና የሬስትሪንት ገቢያቸውም በእጅጉ አየቀነሰ በመምጣቱ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ከኪሳራ ለመዳን ሰራተኞችን ለመቀነስ እንደመገደዱ የሆቴል አሰሪዎች ፌዴሬሽን ለፊደል ፖሰት ገልፇል።
እንደ ኮንፌዴሬሽኑ ገለፃ አብዛኞቹ ሆቴሎች የባንክ እዳ ስላለባቸው በኪሳራ አየሰሩ መቀጠል እንደሚከብዳቸው ተናግሯል።
በኢትዮጵያ ከ600 በላይ ሆቴል ሲኖሩ በኮከብ ደረጃ ግን የተቀመጡት ከ160 አይበልጡም ። የሆቴል መስኩ ከ40, 000በላይ ሰራተኞች እንደያዘ ይገመታል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *