በኢትዮጵያ የገባው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳይባባስ ሰግተናል ያሉ የህክምና ዶክተሮች ፣ነርሶች ፣የህብተረሰብ ጤና አጣባበቅ ባለሙያዎች ፣የስነ ልቦና ባለሞያዎች ፣አዋላጆች ፣ፍርማሲስቶች ያቀፈ ስምንት በጤና ላይ የሚሰሩ የሙያ ማህበሮች ሀሳብ አመንጪ ( think thank) ቡድን በአጭር ቀናት ውስጥ ሊያቋቁሙ መሆናቸውን ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።
ሀሳብ አመንጪ ቡድኑ የኮሮና ቫይረስን ስርጭትን ለመግታት መንግስትና ማህበረሰቡ ምን አይነት መንገድ መከተል አለበት በሚለው ላይ ለመንግስት መፍትሄ ሀሳብ እያቀረበ ይወያያል ሲሉ የሀኪሞች ማህበር ዶ/ር ተግባሩ ዘገዬ ለፊደል ፖስት ገልፀዋል።
” ጊዜው ሁላችንም የምንረባረብበት ጊዜ እንጂ መንግት ላይ ነገሩን ጥለን የምንቀመጥበት አይደለም”
” እንደ ሀኪሞች ማህበር ከሎሎች መሰል ማህበራት ጋር በመተባበር ለጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ ምንነትና ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ስልጠና ከመንግስት ጎን ሰጥተናል ።በቂ ግን አይደለም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ።
” የሀሳብ አመንጪ ቡድንም እያደራጀን ነው በቀጣይ ሳምንት ወደ ስራ ይገባል ። የቡድኑ አላማም ኢትዮጵያ የገባውን ኮሮና ቫይረስ ስርጨቱ ሳይሰፋ እንዴት እንግታው በሚለው ላይ ሀሳብ እያመነጩ መንግስትን ማማከር ይሆናል ” ሲሉ ገልፀዋል።
ዶ/ር ተግባሩ መንግሰት የቫይረሱ ስርጭትን ለመግታት ት/ ቤትን በመዝጋት፣ስብሰባዎችን በመከልከልና እጅን በመታጠብ የጀመረው ተግባር መልካም ቢሆንም ብዙ አስጊ ነገሮች እንዳሉም ጠቁመዋል
” ቫይረሱ የታጨቀ የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ባይፈልግም አሁንም በታክሲ፣በመንገድ፣ በመመገቢያ ስፍራዎችና በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ቢሮዋች ላይ ጥንቃቄ የጎደለው ተግባር እየታየ ነው ። ይሄን ነገር ሊቆም ይገባል ።የመኖርና የአለመኖር ነገር ነውና” በማለት ጉዳዩን አቅሎ ማየት እንደማይገባ አሳስበዋል።
በአሁኑ ሰአት በኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዙ ሰዎች ብዛት ዘጠኝ ደርሷል።