ባለሀብቱ ቀነኒሳ ሆቴልን በከፊል ለሰራተኞቻቸው ማደርያ ሲያረጉ 250 ድሆችን ምሳ የማብላት ሳምንታዊ ፕሮግራም ጀምረዋል

በሃዋሳ ከተማ በስፋት የሚታወቁትና የኦሲስና ሆቴል እና የሉሲ ቡና ላኪ ኩባንያ ባለሃቤት አቶ ብርሀን ተድላ ከጓደኛቸው አቶ ተስፋዬ አለና ጋር በመቀናጀት በኮሮኖቫይረስ ስጋት የወደቁ ድሀዋችን” በአቅሜ መርዳት አለብኝ “ብለው በማሰብ አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ 250 የጎዳና ተዳዳሪዎች እና እንጠጦ አካባቢ በአንድ ቤት ተጠግተው ለሚኖሩ የአዕምሮ ህመምተኞች ከነገ ጀምሮ በየሳምንቱ እሁድ ምሳ አበላለው ሲሉ ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።


ባለሀብቱ ተከራይተው የሆቴል ስራ የሚሰሩትበትን ቦሌ መድሀኒያለም የሚገኘውን የቀነኒሳ ሆቴልን 40 ሰራተኞቻቸውን ከደሞዛቸው ጋር በሆቴሉ ውስጥ እንዲያድሩ እንዲመገቡ ያደረጉ ሲሆን 80 ሰራተኞቻቸውን ደግሞ ከደሞዝ ጋር የአመት እረፍት እንዲወጡ አድረገዋል።


“ህዝብን ሀገርን መውደድ ማለት ችግር ውስጥ ስንገባ በአለን አቅም መረዳዳት ነው ።ያደረኩትን ነገር እንደትልቅ ነገር አላየውም ።ያው የአቅሜን ያክል ለመወጣት በማሰብ ነው “
” ኮሮና የሀገራችን ኢኮኖሚ ፣ማህበራዊ ትስስር እየጎዳ ይገኛል ።እንዲህ አይነት ፈተና ሲገጥመን በመተባበርና በመደጋገፍ ፈተናን ማለፍና ለችግሮች መፍትሄ አየሰጠን ጠንክረን መገኘት ነው ያለብን ።”
” ፈጣሪ ኢትዮጵያን አለምን ከገጠማቸው ፈተና አንዲያወጣን እመኛለው ።” ሲሉ ተናግረዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *