17 አመት በጀርመን የኖረውና እሁድ ህዳር 28 ,2012 አዋሽ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ ጋር ባለ የኤትኤም ማሽን ብር ላወጣ ስል ከባንኩ ጥበቃው ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ግራ እግሬን በጥይት ተመትቻለው የደረሰበኝም ጉዳት ስራ እንዳልሰራ ከቤት እንዳልወጣ አድርጎኛል የሚለው ወጣት ኖቤል ነቢል አሁን ስለሚሰማው ስሜት ለፊደል ፓስት እንዲህ ብሏል ።” መቼም እብድ ካልሆነ በስተቀር በትንሽ አለመግባባት መሳርያ አንስቶ ጥይት ይተኮሰብኛል ብለህ አትጠብቅም።ቀይ ቲሸርት የለበሰ ጥበቃ ዪኒፎርም ያላረገ ሰው ኤትኤም ማሽኑ ጋር ተጠግቶኝ ማውራት ጀመረኝ ።ወሬያችን ወደ ጭቅጭቅ ተቀየረ ።በመጀመርያ ጥበቃም አልመሰለኝም ነበር። ወደ ጥበቃ ቤት መሳርያ ይዞ ሲመጣ ነው ጥበቃ መሆኑን ያወኩት ።ወደ ቤቴ ለመራመድ ሳቀና ግራ እግሬን በጥይት መታኝ ።በእኔ የሆነው ነገር ይሄ ነው ።እጅግ ማዝነው እንኳን ጥይት መቶክ አይደለም በቦክስ ሰውነትክ ላይ ጉዳት ያደረሰ ሰው ሲታሰር ነው ማውቀው ።እኔን በጥይት መቶ እግሬን እንዳይራመድ ያደረገው ሰው ተፈቶ ስታይ ፍትህ የት ነው? ብለክ ትጠይካለክ ። አዋሽ ባንክ ጥበቃቸው እኔ ላይ ስላደረሰው ጉዳት ይቅርታ መጠየቅ ሲገባቸው ይሀው ሁለት ወር ደውለው እንኳን አይዞክ አላሉኝም። እውነት የዘረፋ ተግባር ቢሆን እስከአሁን ክስ ይደርሰኝ ነበር ።ምንም ነገር የለም ቤት ተኝቼ ህመሜን ከማስታገስ ውጪ። ይሄ ነገር ያሳዝነኛል ።እግሬን ሲሻለኝ ክሴን አጠናክሬ ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት በቅርቡ አመራዋለው።” ብሏል
በጉዳዩ ላይ ፊደል ፓስት አዋሽ ባንክ ዋና ቢሮ ሄዳ የህዝብ ግንኙነት ክፍሉን ጠይቃ ነበር ” ጉዳዩ ከወንጀል ጋር ነው ያያዝነው ። ህግ የያዘው ጉዳይ ስለሆነ ዝርዝር ነገር መናገር አንችልም ” ሲል የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ምላሽ ሰጥቷል።