ኢድኬሽን ፈርስት የተባለ ተቋም በ100 ሀገራት ላይ ባሉ በ2.3 ሚልየን ህዝቦች ላይ ባካሄደው ጥናት ኢትዮጵያውያን እንግሊዘኛ ቋንቋን መረዳትና መናገር እንደሚቸገሩ ጠቁሞ በቋንቋውም ለእድገት የሚጠቅሙ ምርምር ጥናትን ማድረግ ክህሎታቸው ዝቅተኛ ነው ተብሏል ። ጥናቱ የኢትዮጵያውያንን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት አወዳድሮ ከ100 ሀገራት 63 ደረጃ አስቀምጧታል። ከእፍሪካ ደቡብ አፍሪካ ፣ኬንያ እና ናይጀርያ የተሻለ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት አላቸው ሲል ቱንዝያ፣ግብፅ እና ሊቢያ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎታቸው ልክ እንደ ኢትዮጵያ ደካማ ነው ብሏል። ዴንማርክ፣ስዊዲን እና ኖርዌይ በደረጃው አናት ናት ላይ በጥሩ ነጥብ ተቀምጠዋል።