የራይድ ትራንስፓርትን በስራ ላይ እያሉ ዘረፋ ወይንም አደጋ ቢደርስባቸው ለፓሊስ፣አቅራቢያቸው ላለ ማህበረሰብ እንዲሁም በቅርበት ላሉ ሎሎች የራይድ ታክሲ ሹፌሮች በስልክ ጥሪ የሚያሳውቅ “ዱካ” የተባለ ሶፍትዌር ለመግጠም የራይድ ትራንስፓርት መስራችና የሀይብሪድ ዲዛየንስ ኩባንያ ሀላፊ ወይዘሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ዱካ ሶፍትዌርን ከገነባው ሆራይዘን ኤክስፕረስ ኩባንያ ጋር የመግባብያ ስምምነት ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራርመዋል።
ሶፍትዌሩን ለማስገጠም 6,500 ብር የሚያስፈልግ ሲሆን ተጠቃሚዎች በአንዴ መክፈል ለማይችሉ በ6 ወር ብድር እንዲያገኙ ለፋይዳ የተባለ ብድርና ቁጠባ ተቋም በጠለፋ ዋስትና ብድር ያመቻቻል ተብሏል።
ይሄ ሶፍትዌር በተጨማሪ የመኪና ጎዞ ክትትል፣የፍጥነት መቆጣጠርያ ጠቋሚ፣የነዳጅና የመኪና ወጪ መከታተያ፣የስራ፣ክልል መገደቢያ፣የኮሮኮንች ላይ መኪና መናጥን ይጠቁማል ተብሏል።