ኮተቤ ኤካ ጠቅላላ ሆስፒታል በCOVID-19 የህክምና ማእከል መለያ ክፍል ውስጥ ገብተው ምርመራና ህክምና እየተደረገላቸው ያሉ ሰዎች በማእከሉ ከፍተኛ የውሃ ችግር አለ አንዳንዴ እጃችንን እንኳን የምንታጠብበት ውሃ እየተቸገርን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለፊደል ፖሰት ተናግረዋል ።
ለፊደል ፖሰት ከደረሱ መልእክቶች መሀል ይሄ ይገኝበታል;
” ከበሽታው ለመጠበቅ በውሃ እና በሳሙና ታጠቡ ብሎ መንግስት ይናገራል እዚህ መለያ ክፍል ውስጥ ያለን ሰዎች ያንን ለማድረግ ውሃ በተደጋጋሚ ጊዜ ስለሚጠፋ በጣም እየቸገርን ነው።”
በጉዳዩ ላይ ለፊደል ፖስት ምላሽ የሰጡት የማእከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ኪዳኔ በተወሰነ መልኩ የውሀ ችግር እንዳለ ገልፀው ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል ።
” ሆስፒታሉ ለኮሮና ቫይረስ ህክምናም ከመዋሉ በፊትም የውሀ ችግር አለበት ።አሁን እንደውም የተወሰነ ለውጥ አለ ።ችግሩን ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጀምሮ ጉዳዮ ለሚመለከታቸው ፌዴራል መስርያ ቤቶች አሳውቀናል ።በቅርቡም ችግሩ መሉ መፍትሄ ያገኛል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ “ተናግረዋል ።