በሰባራ ባቡሩ አልኮል መሸጫ አትራፊዎችን ለመከላከል የገዢዎች ጣት ኮፒ ሲቀባ ታይቷል



ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር ተያይዞ ባለፉት 15 ቀናት በቀን ቢያንሰ 2,000 ሰው ሲያስተናግድ የነበረው ሰባራ ባቡር የሚገኘው ባለ ዛፍ የአልኮልና መጠጥ ፍብሪካ አትርፎ ሻጮች ሲያስቸግሩት በእያንዳንዱ ገዢ ላይ እጅ አውራ ጣት ላይ ኮፒ ሲቀባ ታይቷል።
ይሄ ለምን ሆነ? በማለት ፊደል ፖስት የፍብሪካውን አንዲት ሽያጭ ሰራተኛ ጠይቆ ነበር ።
” አትርፎ ሻጮች ሰሞኑን ከበውን ነበር ።70 ብር የሚሸጠውን አልኮል ከእኛ ይገዙና መልሰው አጠገባችን 300 ብር ድረስ ይሸጡታል ።እኛም አልኮሉ ለሰው እንዲዳረስ በማሰብ አንዴ የገዙ ሰዎች ደግሞ ተሰልፎ እንዳይገዙ የእጃቸውን አውራ ጣትን ኮፒ በመቀባት ደግመው ቢመጡ ቶሎ የመለየት ዘዴን ምርጫ ስንመርጥ እንደሚደረገው ላለፉት አራት ቀናት ተጠቅመንበት ነበር ።
” ሆኖም ግን አንዳንድ ሰዎች የተቀቡትን ኮፒ በኬሜካል በማስለቀቅ ደግመው ለመግዛት ሲሞክሩ አስተውለናል።”
“አሁኑ መሸጥ አቁመናል ።አልኮላችን በሁሉም ክፍለ ከተማ ላይ ባሉ በሸማቾች ማህበር በኩል እንዲሸጥ ተስማምተናል ” ስትል ተናግራለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *