“ሆቴሎች የመጣባቸውን ከባድ አደጋ ለመታደግ ከወለድ ነፃ ብድር ያስፈልጋቸዋል ” ፍትህ ወልደሰንበት
የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጋቢት መጀመርያ መግባቱን ተከትሎ የቀዘቀዘው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከጎዳቸው ዘርፎች መሀል አንዱ የሆቴል አገልግሎቱን ነው ። በስብሰባ በሰው የሚሞሉት አዳራሾች ፣ የመመገቢያ ሪስቶራንቶች ሰው እምብዛም አይታያቸውም ።ይሄም የሆቴል ባለቤቶችን በቀጣይ ምን መስራት እንዳለባቸው ግራ ከማጋባቱ ባሻገር የተወሰኑ ሰራተኞቻቸውን እንዲቀንሱ አስገድዷቸዋል።

ፊደል ፖስት አዘጋጅ ተስፋዬ ጌትነት አቶ ፍትህ ወልደሰንበትን በወቅታዊ የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፍ ተግዳራቶች እና ፌዳሬሽናቸው እየሰራ ስላለው ጠይቀቋቸዋል፡ አቶ ፍትህ ወልደሰንበት የኢትዮጵያ ሆቴሌእና አሰሪዎች ፌዳሬሽንን ከመስራቾቹ እና የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሆነው ላለፉት ሶስት አመታት በመምራት ሊይ ሲገኙ የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፍ ባለሀብቱን በመወከልየተለያዩ ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ሊይ የሚገኙ ሲሆን ፌዳሬሽናቸውም በሀገሪቱ ካለየባለሀብቱ አደረጃጀቶች በጥሩ ሁኔታ እየተቀሳቀሰ የሚገኝ ህብርት ነው፡፡


ፊደል ፖስት: – አቶ ፍትህ የኮረና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ በሆቴልች ላይ ያሳደረውን ተፅእኖ ቢነግሩን?
አቶ ፍትሀ – የሀገራችን ሆቴሌ እና ቱሪዝም ጫና እየባሰበት የመጣው ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ
ነው፡፡ እንደሚታወቀው የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፍ ከጸጥታ እና ሰሊም ጋር ከፍተኛየሆነ ትስስር አለው፡፡ በሀገራችን በነበረው ለውጥ ሂደት አጋጥመው የነበሩ አለመረጋጋቶች የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፉ ሊይ ትልቅ ጫና አሳርፎ ነበር፡፡

ይህበእንዲህ እያለ 2012 ዓ.ም ከመጀመሪያው የበጀት አመት ጀምሮ ጥሩ መነቃቃትእና የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፉም መነቃቃት ጀምሮ ነበር። ይህ በእንዲ እያለ የኮረናቫይረስ ዓለምን ባልጠበቀቸው እና ባልተዘጋጀችበት ከፍተኛ አደጋ ሆኖ መጣ፡፡

ይህ ቫይረስ በባህሪው የሰዎችን የመንቀሳቀስ፤ የመሰብሰብ እና የመዝናናት ክንውኖችን የገደበ ክስተት ሆኗል፡፡ ይህን ተከትሎ ሆቴልች ገበያ ቀዝቅዟል ብቻ ሳይሆን ለመዝጋትም አስገድዷል፡፡ የኮረና ቫይረስ ሆቴሎቻችንን አዘግቷል፤ ገበያ አሳጥቷል፤ ሰራተኞቻችንን ስራ አሳጥቷል ባጠቃላ ይ በሀገራችን ኢኮኖሚ ሊይ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሯል። የወደፊቱንም እንድንተነብይ አድርጎናል፡


ፊደል ፖስት – አንዳንድ ሆቴልች ከገበያ መቀዛቀዝ ጋር ተያይዞ ሰራተኞቻቸውን ሲቀንሱ ፣ያለደሞዝ ፍቃድ ሲያስወጡ ታይተዋል፡፡ አዚህ ሊይ ያሎት አስተያየት ምንድን ነው?

አቶ ፍትሀ – የሆቴሎቻችን ገበያ መቀዝቀዝ ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ እየተዘጉ ነው፡፡በዚህ ምክንያት መንግስት ሰራተኞቻችንን እንዳት በዚህ ወቅት ማስተዳደር እንዳለብን የስራ ላይ ፕሮቶኮሌ አዘጋጅቷል፡፡ ይህም ፕሮቶኮል ከወጣ በኋላ ወዲያው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወጥቷል፡፡ በነበረው የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የድርጅት ስራ ከቆመ እና ስራ ከቀነሰ ሰራተኛ እንዴት እንደምትቀንስ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን ይህ በሀገር የመጣ እና ከፍተኛ የስራ አጥነትን የሚያስከትል ክስተት ስለሆነ ሁለም ጉዳዩን ተረድቶ እንዲተጋገዝ የሚጠበቅበት ጊዜ ነው፡፡

መንግስት አስቸኳይ አዋጁን ሲያወጣ ሰራተኛ ማባረር አትችሉም፤ መቀነስአትችሉም ቢልም የኢፌዴሪ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስቴር በሚያወጣው አዲስ ፕሮቶኮል የወጣ ስላላሆነ በፊት የወጣው ፕሮቶኮል ነው መጠቀም የምንችለው፡፡ በዚህም ፕሮቶኮል ከሰራተኛው ጋር መመካከር፤ እረፍት መስጠት፤ እረፍት፣ባይኖረውም ከሚቀጥለው አመት እረፍት ማበደር፤ ስራ ስለሌ ሆቴሎቹ ከባድ ስለሆነ ደመወዝ እየከፈለ፤ በድርድር እየቀነሱ ከኮረና በኋሊ የስራ ዋስትና እየሰጡ ማስቀመጥ የተፈቀደ ናቸው፡፡

ቅድም እንደገለፅኩልህ የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፍላለፉት አራት አመታት ገበያው በጸጥታ እና ባለመረጋጋት በከፍተኛው በወረደ ሰዓት ሰራተኛውን ሳያባርር፤ ሳይቀንስ የባንክ ብድሩን እየከፈለ የመጣ እና በ2012 ዓ.ም ልከስር ነው ብሎ በሚያስብበት እና ከፍተኛ የካሽ እጥረት በገጠመበት ወቅትነው ኮረና የተከሰተው፡፡ ይህ በመሆኑ አንዳንድ ሆቴልች ሰራተኞቻቸውን ደመወዝ የመክፈል አቅም አንሷቸዋል፡፡ በዚሁ ከቀጠሉ አብዛኞቹም ሆቴልች ይህ ችግር በቅርቡ ይገጥማቸዋል፡፡ ፌዳሬሽናችን እንዱ የሀገሪቱ ሆቴሌ እና ቱሪዝም

ባለቤቶች/አሰሪዎች ወኪሌነቱ ይህንን ሊቀርፍ የሚችል የመንግስት ድጋፍ ይህሳይመጣ በፊት ጥያቄ አቅርቧል፤ መንግስትም ሌክ እንደኛው ይህ ዘርፍ ከፍተኛችግሮች ሉገጥመው እንዯሚችሌ ተንብዩ የተሇያዩ መፍትሄ ሀሳቦች በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡ ይህም በቅርቡ ምላሽ አግኝቶ ይህንን ክፉ ወቅት በጋራ ተረባርበን እንደምንወጣው ባለሙለ ተስፋ ነኝ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ሰራተኞችም የአሰሪዎቻቸውን
ችግር በመረዲት ትንንሽ ጊዜዎችን እና ክፍተቶችን በትግስት በማለፍ ትብብር

እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለው፡፡ ሁለም ባለሆቴሌ ብዙ አውጥቶባቸው አሰልጥኗቸው ያቆያቸውን ሰራተኞቹን እንዱሁ መበተን አይፈልግም፡፡ ሀብቶቹም ናቸው፡፡

ፊደል ፖስት – ከኮረናቫይረስ ጋር ተያይዞ አንዳንዴ ሆቴልች ገበያ ስለቀዘቀዘባቸው ሆቴሎቻቸውን ለመሸጥ ለደላሎች እየነገሩ ነው ፡፡ ይህ ሁኔታ ምን ያመላክት ይሆን;

አቶ ፍትሀ – ዘርፉ የተጠራቀም ችግር አለበት፡፡ ፌዴሬሽናችን ከባህሌ እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አመታዊ የሆቴሌ እና ቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዘጋጀት ጀምረዋል፡፡ ይህ ኮንፍረንስ ዋና አሊማው ዘርፉ ያለበትን ከ መልካም አጋጣሚዎችን እና ተግዳሮቶችን አመልክቶ ተፈጻሚነታቸው በመስራት በከፍተኛ ደረጃ የሚዘጋጅ አመታዊ የምክክር መድረክ ነው፡፡ በመጀመሪያው የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፎች የቀረቡት መሰረታዊ ነገሮች አሁን ባለሀብቱ እንደዚህ አይነት ውሳኔዎችን ሊያስወስነው ይችላል፡፡ አሁን ያልከው መረጃው ባይኖረኝም የሆቴል እና ቱሪዝም ዘረፍ ከፍተኛ ፋይናንስ የሚፈልግ፤ ይህም በብድር የሚገኘው ፋይናንስን ቢዝነሱን ሊመለስ የሚችለው በረጅም አመታት ነው። በኮረና አይነት ክስተት እና በሰላም እና ፀጥታ መጥፋት
ምክንያት ትንሽ ኮሽ ባለ ቁጥር የመጀመሪያው ተጠቂ ዘርፍ ነው እና እጅግ በጣም ሴንሴቲቭ ነው፡፡ ባንኮቻችን እንደሚታወቀው የአገልግሎት ዘርፍ ነው በማለት የሚሰጡት ብድር የ10 በዛ ቢባል የ15 ዓመት ነው፡፡ ይህንን በአጭር ጊዜ ውስጥ
ለመክፈል አሁን ኢትዮጵያ ውድ ሀገር ናት እያስባለ ያለው ከፍተኛ ዋጋ በማስከፈላቸው ነው፡፡ በነዚህ እና ባለፉት አራት አመታትም በነበረው ጫና የዚህ አይነት ውሳኔዎች ቢኖሩ ተጠባቂ ናቸው፡፡ ይህንን ስሜቶች እንዲይኖሩ መንግስትም በተለያዩ እገዛዎች ከጎናቹ ነን ሉለን ይገባል፡
ሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፍ ሁለም ተረባርቦ ቢሰራበት ከፍተኛ የስራ እድል የሚፈጥር፤ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ የሚያመነጭ እና አብዛኛው ዘርፉ የተያዘው በሀገራችን ልጆች በመሆኑ ለኢኮኖሚመረጋጋትም ትልቅ አስተዋጽዎ አለው፡፡

ፊደል ፖስት – አሁን ያለው የሆቴልች የገበያ ችግር ምን አልባት በዝቅተኛ ዋጋ አገልግሎት በመስጠት መቋቋም አንደ አማራጭ ያገለግል ይሆን?

አቶ ፍትሀ – አሁን ያለው የሆቴልቻችን ገበያ ማጣት የዋጋ ጉዳይ አይደለም፡፡ በሀገራችን
የሀገር ውስጥ ቱሪዝም አላደገም፤ የተለያዩ ተያያዥ ጉዳዮች አለበት የሀገራችን የሆቴል ገበያ እስካሁንም የኮንፍረንስ፤ የቱሪስት እና በተለያዩ ስብሰባዎች ምክንያት የሚፈጠር ነው፡፡ እነዚህ እንዲይሆኑ የኮረና ቫይረስ እንዲሁም አስቸኳይ አዋጁም ሰዎችን መንቀሳቀስ፤ መሰብሰብ ከልክሏል፡፡ የኮረናቫይረስ ያለበትም ሁኔትበጥቅሌ ስሊሌታወቀ ሰዎች በቤት መቆየት እና ከእንቅስቃሴ መቆጠባቸው
ጨምሯል፡፡ ገበያው በዚህም ምክንያት ነው እንጂ በዋጋ ምክንያት አይደለም፡፡ ይህሲያልፍ እርግጠኛ ነኝ ሆቴልች በቅናሽ ዋጋ ሊመጡ ይችላሉ፡፡ እስኪ ሚመጣው ውድ ሆቴሌ ይገኝ እና በቅናሽ ማስተናገድ እድለን ባገኘን፡፡ ነገር ግን የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም ግን ግዴ ይሆናል፡፡ አንዳንዴ ሆቴልች የጀመሩትን ባለበት ቦታ ማቅረብ ሊበረታታ የሚያስፈልግ እርምጃዎች ናቸው፡፡

ፊደል ፖስት – ኮረና ቫይረስ መድሀኒት ቢገኝለት እንኳን የሆቴል ገበያ እንደነበረው መመለስ አስቸጋሪ ነው ብለው የሚሟገቱ ሰዎች አሉ፡፡ የእርሶ ሀሳብ በዚህ ላይ ምንድን ነው ?

አቶ ፍትሀ – እንደ ሀገር እያስጨነቀን ያለው ይህ ነገር አልፎ እንዴት ነው የምናገግመው የሚለው ነው፡፡ እኔ አይመለስም ከሚሉት ሳሌሆን ለመመለሻው ጊዜ
ብዙ ስራ የሚፈልግ እና ጊዜ የሚፈጅ ነው፡፡ ምክንያቱም አሇኘለም ከዚህ በኋላእንደድሮው በግሎባላይዜሽን እንደተቀራረበች ትቆያለች ወይ የሚለው ከባድነው፡፡
ሀገራት ቶል በራቸውን ከፍተው ሰዎች እንደልብ ይንቀሳቀሳሉ ወይ ሚለው ከባድ ነው፡፡ ሰዎች ስነልቦናቸው ተመልሶ ለመዝናናት፤ ተዘዋውሮ ለመስራት እምነትበቶል ያገኛሉ ወይ? ከባድ ነው፡፡ ይህንን ስታስብ ማገገሙ ከባድ ነው፡፡ አደጋውን መቀነስ ከማገገሚያ ወጪ ያንሳል በሚል ነው ፌዴሬሽናችን ይህንን ወቅት ተባብረን ተደጋግፈን ማለፍ አለብን የምንለው።

ፊደል ፖስት- መንግስት የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፍን ከኪሳራ ለመታደግ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?

አቶ ፍትሀ – ፌዴሬሽናችን ከመንግስት የተለያዩ እገዛዎችን ጠይቀናል; በአሁን ሰዓት
ከሀገሪቱ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በተጎጂነት በቀዲሚነት ላይ የሚገኘው የሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ነው፡፡ ይህንን መንግስትም ተረዴቶ በተለያዩ አግባቦች ሊያግዘን እየሰራ ይገኛል፡፡ እኛም ሳንሰለች ጉዳያችንን በማስረዳት ምክረ ሀሳቦችን በመስጠት

መንግስትን እያገዘን እንገኛለን፡፡ ይህ ዘርፍ ለመታደግ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች የቅንጡ ጥያቄዎች አይደለም። በጥናት ሊይ የተመሰረተ ማክሮ ኢኮኖሚውንም የሚያግዝ እና አሁን መከላከል በማገገሚያ ወቅት ወጪ መቀነስ ነው በማለት ነው።
የቀረቡት ጥያቄዎች፡፡ ከጥያቄዎቹም ለብዙ አመታት ያበቃናቸው እና ብዙ ወጪ ያወጣንባቸው ሰራተኞቻንን በዚህ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ማጣትአንፈልግም፡፡ መንግስትም በአስቸኳያ አዋጅም ሰራተኞችን መቀነስም ማባረርም እንደማይቻል ወስኗል፡፡ ስለሆነም እነዚህን ሰራተኞቻችንን እንድናቆይ የወርሀዊ ደመወዝ እንድንከፍል የወለድ ነጻ ብድር እንዱሰጠን፤ የሆቴል እና ቱሪዝም ቢዝነስ እንደሚታወቀው እንደሌላ ቢዝነስ ተዘግቶ ማቆየት የማይቻል እና ተከፍቶ እየፀዳ፤የተለያዩ አገልግሎት መስጫዎች እየሰሩ እና የመብራት፤ ውሀ፤ የጀነሬተር ነዳጅ እና የመሳሰሉ መሰረታዊ ክንውኖች ስከማይቆሙ የስራ ማስኬጂያ ብድር ከወዱሁ ነጻ እንዲሰጠን፤ አሁን ሊይ ስራዎችችን 0% እና ወደዛ እየተቃረብን መሆኑ ሆቴሎ ቹ ያለብን ብድሮች ለመክፈል እየተቸገርን ስለሆነ ያለብንን የባንክ ብድር ከነወለዱ ሳይቆጥር ለአንድ አመት እንዲራዘምልን እና በማገገሚያ ወቅትምየመክፍል አቅማችን ቶሎ ስለማይመለስ የብድር መክፈያ ጊዜያችን ዓመቱ

እንዲያራዘምሉን እና ወራዊ ክፍያ መጠኑ ሊቀንስሉን ስለሚችል ማገገሚያ ጊዜው የተሳካ እንዲሆን ስከሚያደርግ፤ በግብር ሊይ ያለ ውዝፍ ክፍያዎች፤ የሰራተኛ ግብር እና የጡረታ መዋጮ እና የመሳሰለ የግብር ጉዲዮች ጊዜ እንዱሰጠን ጠይቀን
መንግስትም ተራ በተራ እየመለሰ ይገኛል፡፡ የግብር ጉዳዮች በአብዛኛውተመልሰዋል፡፡ ነገር ግን ወቅታዊ የሆነው እና ፈጣን ምላሽ ለሚፈልገው የባንክ
ጉዲዮች እንዱመለሱ በቆዩም ቁጥር ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጡ በመሆናቸው ቶሎእንዲፈጸሙ እኛም መንግስትን እያገዝን እየጠየቅን ነው መንግስትም በቅርቡ ምላሽ ይሰጣሌ ብለን ተስፋ አናደረጋለን፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ባፋጣኝ ካልተገኘ የኢንደስትሪ ሰላም፤ የዘርፉ ባለሀብት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እና ቢዝነሶቹ ቶሎ ሉያገግሙ ሚችልበት እድል እየጠፋ ይመጣል እና ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡

ፊደል ፖስት፣ – አንዳንዴ ሆቴሌ ባለቤቶች ሆቴሎቻቸውን በኮረናቫይረስ ለሚመረመሩ ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንዱውሌ አዴርገዋሌ ይህም ከህዝቡ እና ከመንግስት ምስጋናን እንዱያገኙ አድርጓቸዋሌኘል፡፡ የኢትዮጵያ ሆቴሌ ባለቤቶች/አሰሪዎች ፌዳሬሽን ለኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለሚዯረገው ስራ ያበረከቱትን አስተዎፆ እንዴት አዩት?

አቶ ፍትሀ – ፌዴሬሽናችን የሆቴሌ ዘርፍ ሊይ ያሉ ባከሀብት ለሀገራዊ ጥሪ ሁሌም ከፊትእንደሚቀርብ በሙለ ልብ ያምናል፡፡ ሳይጠየቁ ይመለከተኛሌ ብለው ይህንንምያደረጉትን ሀገራዊ ጀግኖች ናቸው ብለን እናምናለን፡፡ ለዚህ ጉዳይ ይዋል ብል መስጠት ብቻ አይደለም ከፍተኛ የሀገራዊ እና ህዝባዊ ሀላፊነትን መወጣት
ነው፡፡ ባለሆቴልቻችን ሆቴላቸውን ብቻ አይደለም እየሰጡ ያለት፤ በካሽ ገንዘብ መንግስትን እየደገፉ ነው ።በአይነትም ትላልቅእገዛዎችን እያደረጉ ነው። ሁሉንም
አብሬ አሳልፋለው ብለው ከ300 እስከ 600 በላይ ሰራተኛ ያላቸው ሆቴልችሰራተኞቻችንን ይዘን እናልፋዋለን ብለው ቀጥለዋል፡፡ በቁጥር ቢሰላ እጅግ ብዙ ሀብቶች ናቸው፡፡ ይህን ወቅት ስናልፈው ፌዳሬሽናችን ትሌቅ አክብሮቱንሚገልፅበበት መድረክ ይኖረዋል፡፡

ፊደል ፖስት: በዚሁ አጋጣሚ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?

አቶ ፍትህ – ነገን ለመኖር ዛሬን በጥንቃቄ እና በተገቢው ማከፍ አለብን ስለሆነም ህብረተሰባችን የሚያልፍ ዝናብ እንዳይመታው በሚለው አባባል መምከር እፈልጋለው፡፡
መንግስት እና ባለድርሻ አካላት የሆቴሌ እና ቱሪዝም ዘርፍን አሁን መታደግ የማገገሚያ ወጪን እና ጊዜን መቀነስ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *