ፕሬዝዳንት ትረምፕ ከስልጣን ለመነሳት በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ አይደሉም ተባለ



የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ዛሬ ጥር 27 ለሊት ስድስት ከሀያ ባደረገው የውሳኔ ምርጫ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ስልጣንን ያለግባብ ተጠቅመዋል፣ የሀገራቸውን ምክርቤት አሰራር ተጋፍተዋል በሚል በዲሞክራታቾች የቀረባበቸውን ክሶች ጥፋተኛ አይሉም የሚሉ የህግ መወሰኘ ምክር ቤት አባላቱ ድምፅ አብላጫ ስላገኘ ከስልጣን የመነሳታቸው ክስ ውድቅ ተደርጓል።
ትረምፕ ከዩክሬን እርዳታ ጋር በተያያዘ በቀጣዮ ምርጫ የሚፎካከሯቸውን ጆን ባይደንን ልጅ ላይ ዮክሬን ባለው ኩባንያው ላይ ምርመራ እንዲያደርጉ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ላይ ግፊት አርገዋል የሀገራቸውንም እርዳታ እንደማባበያ ተጠቅመዋል እንዲሁም ራሽያን በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ እንድትገባ አድርገው ነው በምርጫ አሸንፈው ፕሬዝዳንት የሆኑት ተብለው ነበር በዲሞክራቶች ከስልጣን እንዲነሱ ባለፈው መስከረም ክስ የቀረበባቸው።
ሴኔቱ የግራ ጎኑን ክርክክር ለወራቶች ከሰማ በኋላ ስልጣን አላግባብ ተጠቅመዋል በሚለው ክስ ላይ 52 ተቃውሞና 48 ድጋፍ እንዲሁም በ የሀገሪቱን ምክርቤት አሰራር ወደ ጎን ትተዋል በሚለው ክስ ደግሞ በ53 ተቃውሞ በ47 ድጋፍ ጥፋተኛ አይደሉም ተብለዋል።
ከምርጫው በፊት ሪፐብሊኩ ሚት ሮምኒ” እኔ ሀይማኖተኛ ነኝ ።ልቤን ሀሳብ እከተላለው ትረምፕ ከስልጣን መነሳት አለባቸው በማለት ” በሰኔቱ ፊት ቀርበው ንግግር አድረገዋል ። ሮምኒ በአሜሪካ ታሪክ የራሳቸውን ፓርቲ ሰው ከስልጣን ይወረድ ሲል የመጀመሪያው ሰው ናቸው።
ለሁለት ሳምንት የትረምፕ የስልጣን መነሳትን በሪፐብሊካንና በዲሞክራት መሀል የነበረውን ክርክር ሲዳኙ የነበር ጆን ሮበርትስ ሁለቱንም ወገን ለነበራቸው ትእግስት አመስግነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *