በአዲስ አበባ በቀን 34 ጥንዶች ጋብቻ ይፈፅማሉ ።ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በግማሽ ቀንሷል



ከሀምሌ አንድ 2011 አስከ ታህሳስ 30,2012 ባሉ ስድስት ወራት ውስጥ አዲሱ ገበያ ሸገር መናፈሻ በሚገኘው የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ 6,124 አዲስ ተጋቢዎች የጋብቻ ሰርተክፌት መውሰዳቸውን ኤጀንሲው ለፊደል ፓስት ገልፇል። በተመሳሳይ ወቅት 432 ጥንዶች “አብሮ መኖር ይብቃን ።ተለያይተን ብንኖር ይሻላል ።”ብለው የፍቺ ሰርተክፌት ወስደዋል።
ይሄ ቁጥርም በአማካኝ ሲሰላ በበጀት አመቱ ስድስት ወር ውስጥ በአማካኝ በቀን 34 ሰው ጋብቻዎች ሲፈፅሙ ከሁለትአስከ ሶስት ጥንዶቸ ደግሞ የፍቺ ሰርተክፌቶች ይወሰዳሉ ማለት ነው ። በ2011 በቀን 77 ጥንዶች ሲጋቡ አራት ጥንዶች ደግሞ በየቀኑ ወሳኝ ኩነት ፊት ቀርበው የፍቺ ሰርተክፌት ይወስዱ ነበር ። ይሄ ቁጥር ኤጀንሲውን ሳያሳውቁ የሚጋቡትንና የሚፋቱትን አይጨምርም ። የኤጀንሲው መረጃ ባለሙያ መአዛሽ ገዝሙ ለፊደል ፓስት እንደተናገረችው የፍቺና ፣የጋብቻና የሞት ሰርተክፌት የማውጣት ባህል አሁንም ቢሆን ብዙ እንዳላደገ ገልፃለች።
” ወሳኝ ኩነት ሰርተክፌት ያላገኙ ብዙ ጋብቻዎችና ፍቺዎች አሉ ።ይሄ ጠቃሚ ሰርተክፌት ነው ኑ እና ውሰዱ ተብሎ ቅስቀሳ ቢደረግም የታሰበውን ያክል ለውጥ አልመጣም። በባለፈው አመት የሞት ሰርተክፌት የተሰጠው 4,340 ብቻ ነው ።ይሄም ቸልተኛነታችን ያሳይል ተብሏል።
ለጋብቻው መቀነስ ምክንያቱ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ መአዛሽ ስትመልስ ” ይሄ ትልቅ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎችን ምርምር የሚጠይቅ ስራ ነው ።እኔ ይሄ ነው ማለት አልችልም ” ብላለች ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *