የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ የጥቁር ገበያውን ዶላር ምንዛሬ ቀንሶታል


ከሳምንታት በፊት የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ በኢትዮጵያ ህጋዊ ባልሆነው ጥቁር ገበያ 42 ብር ድረስ የሚመነዘር ሲሆን ወደ ቻይና ዶላር ይዘው እቃ ለማምጣት የሚሄዱ ነጋዴዎች ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጋር ስጋት ስለገባቸውና የሚያደርጉትም ጉዞ በመቀነሱ ምክንያት የዶላር ፍላጎት በተወሰነ መልኩም ቀንሷል። በዚህም ምክንያት የአንድ ዶላር መሸጫ ዋጋ በሁለት ብር ቀንሶ በጥቁር ገበያው አርባ ብር አየተሸጠ እንደሚገኝ ፊደል ፓስት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በባንኮች ደግሞ የዶላር ምንዛሬ ከሁለት ወራት በፊት በየቀኑ አምስት ሳንቲም እየጨመረ ከ32 ብር አልፎ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ዝቅ ብሎ 31. 70 አሰከ 31. 90 ከፍና ዝቅ አያለ ባለፉት ሁለት ሳምንት አየተሸጠ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *