ኮሮናን ለመግታት እጅ መታጠቢያ በመኪናው የገጠመው ኢትዮጵያዊ ስራውን ለገበያ ሊያቀርብ ነው


ኮሮና ኢትዮጵያ ገባ ከተባለ ጀምሮ በመኪናው ላይ እጅ መታጠቢያ ገጥሞ በአዲስ አበባ እየተዘዋወረ ከ10,000 በላይ ሰዎችን እጅ ያስታጠበው በአዲስ አበባ የሚኖረው ወጣት ዮሴፍ አርካ በሌሎች መኪና ላይ መታጠቢያ ለመግጠም የትራንስፖርት ሚኒስቴርን ፍቃድ እንደጠየቀ ለፊደል ፖስት ተናግሯል።



” ሰሞኑን ሀገሬ ላይ የገባው ኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሰዎች እጃቸውን እንዲታጠቡ ትንሽም ብትሆን የበኩሌን ሀላፊነት እየተወጣው እንዳለ ይሰማኛል ።ጤና ሚኒስቴርም ስራዬን ወደውት በየቦታው ሄጄ እንዳስታጥብ ፈቅደውለኛል “

“ይሄን በመኪና ጀርባ ባለ ጎማ ከፍ ብሎ የተገጠመውን መታጠቢያን በሌላም መኪና ላይ ማየት እፈልጋለው ።ለዚህም ስራ መንግስትን ቦታና ፍቃድ እንዲሰጠኝ እየጠየኩ ነው ። መታጠቢያው ከ20 እሰከ 80 ሌትር ውሃ ይይዛል ።ይሄም ውሃ በሌለበት አካባቢ ስንሆን መታጠቢያ ዉሀ እንዳይቸግረን ያረጋል ”

” ኮሮና የጊዜ ጉዳይ እንጂ መጥፋቱ አይቀርም ። ነገር ግን ሰው እጁን መታጠብ ቢፈልግ ከተማችን ውስጥ እንደ ልብ ውሃ አይገኝም ።ስለዚህ መኪኖች እጅ መታጠቢያ ቢኖራቸው የመኪናው አሽከርካሪም ሆነ ሌላንም ሰው እጅ ማሰታጠብ ይችላል ።እጃችን ታጠብን ማለት ደግሞ ከብዙ በሽታ ተጠበቅን ማለት ነው።”
ሄኖክ ከዚህ ቀደም በዱባይ የኖረ ሲሆን በእንጨት ስራ ላይ ረጅም ጊዜ ሰርቷል።ከአድማስ ዩንቨርስቲም በሰው ሀብት አስተዳደር ተመርቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *