በሆቴልና ኢንደስትሪ ላይ የተሰማሩት አቶ አይሸሹም ተካ ዛሬ 200 የሰውነት ሙቀት መለከያዎችን ከጓደኞቻቸው ጋር በመቀናጀት ከውጭ አስመጥተው ለዘጠኙ የክልልየጤና ቢሮ ተወካዮች ዛሬ አሰረክበዋል።
ከቻይና የመጡት የሙቀት መሳርያዎቹ ዋጋ በብር ሲተመን ሁለት ሚልየን ብር ያወጣል።
በርክክቡ ወቅት አቶ አይሸሹም እንዳሉት

” የንግዱ ማህበረሰብ ወቅቱ ነግዶ የሚያተረፍበት ሳይሆን፤ ወገን እና ሃገርን ከኮሮና ወረርሽኝ ተረባርቦ የሚያተርፍብት ሊሁን ይገባል
ነግዶ ለማትረፍ የሚቻለው ከምንም በላይ ወገን እና ሃገር በጤና ውለው ማደር ሲችሉ ብቻ ነው ።
“በዚህ ወቅት የተጋረጠብን ስጋት በሃገር እና በወገን ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እና ጥፋት አሳሳቢ ነው። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት በመፍራት ሳይሆን በብልሃት፤ በመጨነቅ ሳይሆን በመጠንቀቅ፤ በእየለቱ በዜና በምንሰማው ቁጥር ሳይሆን አደጋውን በመቆጣጠር . እንደምንሻገረው አምናለሁ።”
“የሃያላን ሃገራት በርካታ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ምድር ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በተቻለ ዓቅም ለመቀነስ፤ የንግዱ ማህበረሰብ የመንግሥትን ጥረት በባለቤትነት ስሜት መደገፍ አለብን።”
“ሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከገጠማት ፈተና እንድትወጣ፤ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ሳይንሳዊ የጥንቃቄ መመሪያዎች ህብረተሰቡ በማስተዋል ተግባራዊ ማድረግ አለበት።”
“የተደቀነብብንን ስጋት የሚያሳጣንን ብቻ ሳይሆን ያመጣልንን ዕድል ማስተዋል ይገባል። በትውልድ ሰንሰለት በተግባር ተፈትነው የነገሱ ኢትዮጵያዊ እሴቶችን በትኩረት እና በአፅንዖት ለመተግበር ወገን ለወገን የመደጋገፍ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን መገዘብ ያሻል።”
” በዘመን የገጠሙን ስጋት እና አደጋዎችን የቀደሙት አባቶችና እናቶች ሀገርን በጥበብ አሻግረው አስረክበውናል። እኛም ከመጣብን ፈተና ሃገር እና ወገንን ለመታደግ መደጋገፍ ይኖርብናል።ዛሬ አቅም የፈቀደውን መደገፍ፤ ለነገ ዓቅምን አሟልቶ የሚደግፍ ትውልድና ሃገር ለማስቀጠል የምንረባረብበት ጌዜ ነው ።እኛም ይሄን መሳርያ ስናበረክት በቂ ነው ብለን አስበን ሳይሆን የአቅማችንን ለመወጣት ነው ” ብለዋል።