አዘርባጃን አፍሪካውያን በአርሜኒያ ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበች


ዓለም ግጭቶችን ጨምሮ በተለያዩ አደጋዎች ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው የጠፉ ሰዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ዘክሮ የሚውልበትን ቀን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባ የሚገኘው የአዛርባጃን ሪፐብሊክ ኤምባሲ እኤአ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ በአርሜኒያ ወረራ ወቅት እንደጠፉ የቀሩ 4000 ዜጎቹን በተለይም ለአፍሪካውያን አስታውሱልኝ ብሏል::
በኢትዮጵያ የአዘርባጃን ኢምባሲ የኤምባሲ ጉዳዮች ተወካይ እንደሆኑት እንደ ሩስላን ናሲቦቭ ገለጻ አርሜኒያ የዓለም አቀፍ ህግጋቶችን ችላ በማለት ያገተቻቸው 297 ሕፃናትን ፣ 98 ሴቶችን እና 112 አዛውንቶችን ጨምሮ 267 የአዘርባጃን ሲቪሎች እስካሁን ድረስ አልተለቀቁም:: ይህ የአርሜኒያ ድርጊት እ.ኤ.አ በ1960 ስምምነት የተደረሰበትን የጄኔቫ ኮኔቬንሽንን የጣሰ እና የጦር እሰረኞችን እና ሰላማዊ ሰዎችን አያያዝ ህግ ያላከበረ እና አርመኒያ አዘርባጃን ላይ በደል መፈፀሟን የሚያሳይ ነው“ ብለዋል ሩስላን::
በአዘርባጃን ሪፐብሊክ የጦር እስረኞች ፣ ታጋቾች እና የጠፉ ሰዎች ግዛት ኮሚሽን በሪፖርቱ እንዳለው ከሆነ 36 ልጆች እና 65 ሴቶችን ጨምሮ 196 የኾጃሌ ከተማ ነዋሪዎች በወታደራዊ ኃይሎች በተፈጸሙ ወንጀሎች ጠፍተዋል። እ.ኤ.አ. የካቲት 25-26 ፣ 1992 በአንድ ምሽት ብቻ 613 የኾጃሌ ነዋሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው አርሜኒያ 16 ሕፃናት እና 22 ሴቶችን ጨምሮ ከ196ቱ ጠፍተው ከነበሩት ውስጥ 95ቱ በኾጃሌ በወታደራዊ ኃይሎች ታግተው እንደነበር እማኞች ነበሩ::


“የአዘርባጃን መንግስት ስለ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የአለም አቀፍ አካላት ለማስረዳት አስፈላጊውን እርምጃ ወስዷል። በግጭቱ ምክንታት የጠፉብን ዜጎቻንን ስም ዝርዝር የሚያሳይ መረጃ በአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አማካኝነት ለአርመኒያ ሰጥተናል:: በተጨማሪም የጠፉትን ሰዎች ለማግኘት እንዲረዳ የዘመዶቻቸውን ዲኤንኤ ከአለም አቀፍ ኮሚቴው እንዲሰበስበ አግዘናል።ዘመዶቻቸው የጠፉባቸውን ሰዎችን ለማግኘት አሁንም ድረስ ናፍቀዋል “ሲሉም ገልፀዋል።
ባለፈው መኸር የ 44 ቀናት ጦርነት ወቅት የአዘርባጃን ግዛቶች ከአርሜኒያ ወረራ ነፃ መውጣታቸው ወታደራዊ ግጭቱን አቁሞ የጠፉ ሰዎችን ዕጣ ፈንታ የመለየት እና የብዙ ሺህ ሰዎችን ህመም እና ጭንቀት ወደ ሦስት አሥርተ ዓመታት የሚጠጋ ሥቃይን እና ጭንቀትን ለማስታገስ ሥራን ማከናወን አስችሏል።


አዘርባጃን ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚሽን ጋር በመተባበር ነፃ በወጡት ግዛቶች ውስጥ በስም ባልታወቁ የመቃብር ሥፍራዎች በመሄድ ጭምር የ ሰዎችን የመለየት ስራ ጀምራለች ብለዋል።
እንደ ተወካዩ ገለፃ አዘርባጃን በዓለም አቀፍ ደረጃ የጠፉ ዜጎቿ ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ትኩረትን እንዲስብ፣ በተጎዱ ሰዎች በተባበሩት መንግስታት ጋር በመሆን ዋና ስፖንሰር ሆና እየሰራች ነው ያሉት ወኪሉ ሃገራቸው የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ሁኔታ ኮሚሽን “በትጥቅ ግጭቶች የታሰሩትን ጨምሮ ሴቶችን እና ሕፃናትን ማስለቀቅ” የሚለው ውሳኔ በገንዘብ ትደገፋለች ብለዋል ።
ኤምባሲው አፍሪካውያን ስለጠፉ ዜጎች በሚደረገው ፍለጋ ከአዘርባጃን ጋር እንዲቆሙ የጠየቀው የአዘርባጃን የህዝብ ቴሌቪዥን ዘጋቢ ፊልም በሳየው “በቼሪ ዛፍ ስር ያለው መቃብር” በሚል ስለ አንድ ቤተሰብ አንድ አሳዛኝ ታሪክ በሺዎች የሚቆጠሩ ግፎች ስለተፈጸሙበት ሁኔታ ካሳየ በኋላ ነው።
ዘጋቢ ፊልሙ በጦርነቱ ከተፈናቀለው ካጋኒ የ 7 ዓመቱ ልጁን ኒጃትን መቃብር ከ 28 ዓመታት በኋላ ለመፈለግ ሲሄድ ወታደሮች ይዘውት ጠመንጃ ሲደቅኑበት ልጄን በቤቱ ወደ ሚገኘው የአትክልት ስፍራ አንዲቀብር ሲለምናቸው ያሳያል።

ሩስላን የአርሜኒያ ተጠያቂነት ዓለም አቀፍ ኃላፊነት በቂ ካሳ የመስጠት ግዴታን ጨምሮ የሕግ ጉዳዮችን ትጠየቅበታለች ብለዋል።
ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የጠፋውን የአዘርባጃን ዜጎችን በተመለከተ ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦች በብሔራዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃዎች ላይ ሌሎች ማዕቀቦች እንዲጣል ስራ ይሰራል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *