“ትረምፕ ያቆመውን የገንዘብ ድጋፍ ለመቀጠል ያጤነው ይሆናል ።” ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም


የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እሮብ ማምሻውን ከስዊዘርላንድ ጄኔቭ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሀገራቸው ለጤና ደርጅቱ የምትሰጠውን ድጋፍ ማቋረጡ መልሶ አጢነውት ወደ ቀድሞ ድጋፍ የመስጠት ሁኔታ ይመለሳል ብለው ተስፋ አንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
” በዚህ ወቅት የአለም ጤና ድርጅትን መርዳት በጣም ጠቃሚ ነገር እንደሆነ አሜሪካ ታምናለች ።ለሌላም ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለራሳም ደህንነት ስትል ” በማለት አስረድተዋል።

አሜሪካ የአለም ጤና ድርጅት ስለቫይረሱ በቂ መረጃ አልሰጠም የቻይናን ጥፋት ደብቋል ብላ በአመት ለድርጅቱ አስከ 500 ሚልየን ዶላር የምተሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ማቋሟ ይታወሳል።


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፕዮ ” ቻይና በወቅቱ ለአለም ጤና ድርጅት ስለቫይረሱ ሪፖርት አላደረገችም ” በማለት ስለሰጡት አሰተያየትም ተጠይቀው ነበር ።
” እኛ ከቻይና ውጪ በአለም ላይ 81 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው አንድም ሰው ሳይሞት ነበር ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ብለን ያወጅነው ” ብለዋል። የድርጅቱ ዳይሬክተር
ዶ/ር ቴድሮስ አክለውም ኮሮናቫይረስ ከአለም ህዘብ ጋር ለረጅም ጊዜ ይቆያል ብለዋል።
” በአፍሪካ ፣በደቡብና ሰሜን አሜሪካ ገና ጅማሮ ላይ ነው ያለው ቫይረሱ ምንም እንኳን በተወሰኑ አውሮፓ ሀገሮች መቀዛቀዝ ቢያሳይም ” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *