አሜሪካ ለቀጣይ ሁለት ወራት በቋሚነት ለመኖር መምጣትን ትረምፕ ይከለክላሉ ተብሎ ይጠበቃል



የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “የአሜሪካ ዜጎች ቅድሚያ ስራ ማግኘት” አለባቸው በማለት ወደ ሀገራቸው ‘ግሪን ካርድ ‘ወይንም ቋሚ የመኖርያ ፍቃድ ለማግኘት የሚመጡ ሰዎችን ለቀጣይ ሁለት ወራት አሜሪካ መግባት የሚከለከሉበት ሰነድ እንዳዘጋጁ የተናገሩ ሲሆን እሮብ ሚያዘያ 14,2012 የመመርያው ሰነድ ላይ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ሬውተርሰ ዘገባ ትረምፕ ሀገራቸው ለጊዜያዊነት ለመቆየት የሚመጡ ዜጎቸን እንድትምቀበል ገልፀው ሰልሳ ቀን ሲሞላቸው ግን ቀጣይ ቆይታቸው ይገመገማል ብለዋል።
ትረምፕ ቆሚ ነዋሪ ለጊዜው የሚከለክሉበትን ምክንያት ሲያስረዱ ” በኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያችን ተጎድቷል። ብዙም ሰው ስራ አጥቷል ።ስለዚህ ሌላ ቋሚ ነዋሪ ከማምጣታችን በፊት በቅድሚያ ለሀገራችን ዜጋ ስራ መስጠት ” አለብን ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *