ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኮሮና ቫይረስ የተገኘባት ሴት አለች?



ትናንት ቅዳሜ ማታ በማህበራዊ ሚዲያ ሽሮ ሜዳ በሚገኘው ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኮሮና ቫይረስ የተገኘባት ሴት ተገኘች የሚለውን ወሬ ለማጣራት የሆስፒታሉ አስተዳደር ከፍል ጋር ፊደል ፖስት ደውሎ ያገኘው መልስ ይሄን ይመስላል ;
” ሴትዮ የኤች አይ ቬ እና የአኔሚያ በሸታ እንዳለባትና የኮሮና ምልክት ስለታየባት ደሟ ለህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተልኮ ሆስፒታሉ ውጤት በመጠባበቅ ላይ ነው ።ለጥንቃቄም ሲባል ከበሽተኛዋ ጋር ንክኪ የነበራቸውወደ 22 የሚጠጉ ነርሶች ፣ዶክተሮች እና አስታማሚዎች መለያ ክፍል ውስጥ ገብተዋል።”
የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለፊደል ፖስት እንዲህ አይነት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚነገር ነገር በጤና ሚኒስቴር እና በኢንስቲትዩት ብቻ እንደሚገለፅ ገልፆ ህብረተሰቡ በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይወናበድ ተናግሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *