ራይድ ትራንስፓርት ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት መግቻ ሁለት ሚልየን ብር መደበ



ራይድ ትራንስፖርት ካምፓኒ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሁለት ሚሊዮን ብር ተጠባባቂ ፈንድ መመደቡን ለፊደል ፖስት አሳውቋል።

በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ ሰዎች በሚሰሩበት ምርመራ ጣቢያ ወይም የህክምና ተቋም ከተገኘ ወዲያው support@ride8294.com ጥቆማ አንዲሰጡም ጠይቋል ።

የራይድ አሽከርካሪዎች በበሽታው ከተጠረጠሩ ንክኪ ያረጉባቸውን ቦታዎች ሁሉ በአፋጣኝ ምርመራ እንዲደረግባቸው ከበሽታ ቁጥጥር ጣቢያዎች ጋር አንደሚሰራም ራይድ ትራንስፖርት መስራች ወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ተናገራለች።
” የመፍትሄው አካል ሁላችንም ነን ። ሀገር ከቫይረረሱ ቶሎ ነፃ መውጣት አለባት ።የአንዳችን ስህተት ለሁላችን ጠንቅ የሁላችን ጥንቃቄ ለእያንዳንዱ ሰው መፍትሄ ነውና የጤና ባለሙያዎችን የሰጡንን ምክር በመፈፀም ስርጭቱን ማቆም አለብን። ።እጃችንን በሳሙና መታጠብ፣ ከተጨናነቁ ቦታዎች መራቅ እና መሰል ከቫይረሱ ከሚያጋልጡን ነገሮች መቆጠብ አለብን ስትል ” ሳምራዊት አሳስባለች ።

የራይድ አሽከርካሪዎችም ስራቸው ከሰው ንክኪ ጋር የተገናኘ ስለሆነ በጥንቃቄ ስራቸውን ማከናወን እንዳለባቸው ተናግራለች።

ራይድ ትራንስፖርት ከ11,000 በላይ ሜትር ታክሲዎችን በአዲስ አበባ ላይ በቴክኖሎጂ ደግፎ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *