ጥቁሩን አሜሪካዊን ጆርጅ ፍሎይድን ገድለሀል ተብሎ ክስ የቀረበበት ፖሊስ ጥፋተኛ ተብሎ በፍርድ ቤት ተፈረደበት

የቀድሞ የሚኒያፖሊስ የፖሊስ አፊሰር የነበረው ነጩ ደሪክ ቻቩኒ በጥቁር አሚሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድን ከመኪና ጎማ ስር በማጋደም እና በጉልበቱ አንገቱ ላይ በመቆምና በመግደል በሁለተኛ ደረጃ ያልታቀደ ግድያ ፣ሁለተኛ ደረጃ ግድያ እና ሶስተኛ ደረጃ የሰውልጅን አሰቃይቶ በመግደል ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን በቀረረበበት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ጥፋተኛ ተብሎ ተፍርዶበታል ሲል አርቲ ሚዲያ ዘግቧል።
የፍሎይድ ጠበቆች ፖሊሱ በጉልበቱ ስለረገጠው ትንፋሽ አጥሮት ሞቷል ሲሊ ደሪክ ቻቩኒ ጠበቆች ደግሞ ፍሎይድ የሞተው ሰውነቱ ውስጡ በነበረው ዕፅ ምክንያት ነው ብለዋል ሆኖም ፍርድ ቤቱ ደሪክ ቻቩኒ በቀረበበት ሶስቱም ክስ ጥፈተኛ ነክ ብሎታል ።

ደሪክ ቻቩኒ እስከ 40 አመት የሚጠብቅ እስር ይገጥመዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ደሪክ ቻቩኒ ጆርጅ ፍሎይድን ሲጋራ ለመግዛት ሀሰተኛ የ20 ዶላር ቢል ተጠቅመሀል በሚል ዘጠኝ ደቂቃ ሙሉ ፍሎይድ አንገት ላይ በጉልበቱ ቆሞበታል ይሄም ፍሎይድን ትንፋሽ አሳጥቶ ለሞት ዳርጎታል የሚል መረጃዎች ወጥተውበታል።
ከክስተቱ በኋላም” የጥቁር ሒወት ግድ ይሰጠናል ” ብላክ ላይቭ ማተርስ የሚል ዘመቻ በአለም ላይ በስፋት ታይቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *