ፊደል ፖስት ከአዲስ አበባ አጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ባገኘው መረጃ መሰረት አምና ተገምገምው ለትምህርት ማስተማር በቂ ነገር ባለሟሟላታቸው በዘንድሮ አመት 91 መንግስታዊ ያልሆኑ ት/ ቤቶችን የስራቸውን ፍቃድ ተሰርዟል።
ከነዚህ ውስጥ 55ቱ ቅድመ መደበኛ ፣32ቱ የመጀመርያ ደረጃ አንዲሁም ሶስቱ ሁለተኛ ደረጃ የመሰናዶ ት/ ቤቶች ናቸው።
አንዲሁም በዘንድሮ አመት በከተማዋ 23 አዲስ የግል ት/ቤቶች ሲከፈቱ 15ቱ ቅድመ መደበኛ ፣7ቱ የመጀመርያ አንዱ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ የመሰናዶ ት/ ቤት ነው።
65 ት/ ቤቶች ደግሞ ተገምግመው ለዚህ አመት በማስጠንቀቂያ የታለፉ ሲሆን የሚጠበቅባቸውን መስፈርት ካላሟሉ በቀጣይ አመት ወደ ማስተማር አይገቡም ተብሏል።
በአዲስ አበባ ከ1,700 በላይ የግል ት/ቤቶች ሲኖሩ ት/ቤቶቹ በቦታ ጥበት ምክንያት በቂ ላይበረሪ ፣ላብራቶሪ ፣የስፖርት መጫወቻ ሳይሟሉ ሲያስተምሩ ይስተዋላል።