በሟቿ ዳኛ ሩት ባደር ከሳምንት በላይ የ ክፍት የነበረውን የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ዋና ዳኝነትን ቦታን የ48 አመቷ ሴት ዳኛ ኮኒ ባሬትን አንዲይዙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ መምረጣቸውን በሮዚ መናፈሻ ላይ ቅዳሜ እኩለ ለሊት አቅራቢያ በነበረ ፕሮግራም ላይ ተናግረዋል።
” ባሬት ለስራው ብቁ ናት ። ህገ- መንግስታችንንም አንደተፃፈው አየተረጎመች ታገለግለናለች” ብለዋል
የኒው ኦርሊያንስ ተወላጅ የሆኑት ባሬት ችካጎ በሚገኘው 7ኛ የአሜሪካ ሰርኪዩት ይግባኝ ፍርድ ቤት እያገለገሉ የነበረ ሲሆን ለአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሪነት ዳኝነት እስከዛሬ ከተመረጡ ሰዎች መሀል በሀርቫርድ ወይም በያሌ ዩንቨርስቲ ያልተማሩ የመጀመሪያ ዳኛ ይሆናሉም ተብሏል።