የዚምቧቤ መከላከያ ሚኒስትር ኮሮና ቫይረስ “ነጮች ስለበደሉን የመጣባቸው ቁጣ ነው “ብለዋል



ባለፈው ቅዳሜ ከሀገራቸው ጋዜጠኞች ስለ ኮሮና ቫይረስ የአለም ዓቀፍ ስጋት የተጠየቁት የዝምቧቤ መከላከያ ሚኒስትር ኦፓ ሙቹንግሪ ሲመልሱ ” ኮሮና አሜሪካና አውሮፖ እኛ ላይ ማእቀብ ጥለው ስላሰቃዩን አምላካችን ያመጣባቸው ቁጣ ነው ። እኛ በኢኮኖሚ ቀጥተውን ሲያስጨንቁን ነበር አሁን ደግሞ እነሱ በኮሮና እየተጨነቁ ነው ።” ብለው በመቀጠልም “ዶናልድ ትረምፕ እሱ አምላክ አለመሆኑን ኮሮና አሳይቶታል ” በማለት አነጋጋሪ የሆነ መልስ ሰጥተዋል ።

በዝምቧቤ የህግ ፕሮፌሰር የሆኑት አሌክስ ማጋሳ በሚንስትሯ መልስ እንዳፈሩ ገልፀው ” እንዴት ከአንዲት ሚንስትር የዚህ አይነት አፀያፊ ቃላት ይወጣል? ” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *