የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ

ከሁለት አመት ጦርነት በኋላ  የኢትዮጵያ መንግስት  የትግራይ ክልልን ከሚያስተዳድረው ህወሓት ጋር  የተኩስ አቁም ስምምነት ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ  ከ 9 ቀን ውይይት በኋላ አድርገዋል።

ከአደራዳሪዎች መሀል የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት እንደገለፁት በኢትዮጵያ መንግስት እና በ ህውሓት መካከል የተደረገው  የተኩስ አቁም ስምምነት  ሀፈሪቱን ወደተሻለ ምዕራፍ   ይወስዳታል ብለዋል።

የናይጄሪያ ፕረዚዳንት ኦሊሴንጎ አባሳንጆ ተኩስ አቁም ስምምነቱ ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳ ነውና ቅድሚያ ሰጥተነዋል ብለዋል። በሌሎች የድርድር እጀንዳዎች ላይ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ አልሰጡም

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተደራዳሪ የነበሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምእራባውያን በድርድሩ ላይ ያልተገባ ጫናን ለማሳረፍ ቢጥሩም ከአፍሪካውያን ወንድሞቻችን ጋር ድርድሩን የተሳካ ለማድረግ ሰርተናል ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የጦርነቱ መቆም ለትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ለኢትዮጵያን የተሻለ ጥቅም እንደሆነ ተናግረዋል።  ድርድሩም በፍጥነት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተስፋቸውን ገልፀዋል

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የደረሱባቸው ተጨማሪ የስምምነት ነጥቦች

🔴  “በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ  ሕገ መንግስት መሰረት፤ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ  ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ እናረጋግጣለን። በዚህም ኢትዮጵያ ያላት አንድ የመከላከያ ኃይል ብቻ ነው።”

🔴   “በመሬት ላይ ያለውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ የህወሓት ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ እንዲበተኑ ማድረግ እና እንደገና መዋሃድ በሚያስችል ዝርዝር መርሃ ግብር ላይ ተስማምተናል”

🔴   “በትግራይ ክልል ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ወደነበረበት መመለስን ጨምሮ የሽግግር እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰናል።”

🔴  “ሁሉንም አይነት ግጭቶች እና ጠብ አጫሪ ፕሮፖጋንዳዎች ለማቆም ተስማምተናል። መግለጫ የምንሰጠው የስምምነቱን አፈጻጸሞች አስመልክቶ ብቻ ይሆናል። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ይህን ስምምነት እንዲደግፉ፣ ከፋፋይ እና የጥላቻ ድምጾችን እንዲያቆሙ፣ ለኢኮኖሚ ማገሚያ እና የህብረተሰብ ትስስርን መልሶ ለመገንባት የሚውሉ ሃብቶችን እንዲያሰባስቡ እናሳስባለን።”

🔴  “የኢትዮጵያ መንግስት የህዝብ አገልግሎቶችን ወደነበሩበት ለመመለስ እና በግጭቱ የተጎዱ ማህበረሰቦችን መሰረተ ልማቶች ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረት ይቀጥላል። ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት፣ ገበሬዎች እና አርብቶ አደሮች ወደ ማሳቸው፣ የመንግስት ሰራተኞች ወደ ቢሯቸው መሄድ ይኖርባቸዋል። ይህን በተቀላጠፈ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት የህዝብ ድጋፍ ይፈልጋል። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ እና ተስፋ ሰጪ ምዕራፍ ነው።”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *