የኳታሩን አለም ዋንጫው በማስመልከት በስድስት የአለማችን ከተሞች የደጋፊዎች ፌስቲቫል ይካሄዳል

የ2022ቱን የኳታር የዓለም ዋንጫ ፤ የፊፋ ፋን ፌሰቲቫልን ለማዘጋጀት ከተመረጡት ከተሞች አንዷ ዱባይ ስትሆን ዱባይ ሀርበር በተባለው ቦታ የባህር ዳርቻ አካባቢ 330 ካሬ ስፋት ባለው ግዙፍ ስክሪን በ4D ድምፅ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከህዳር 11 ጀምሮ – ታህሳስ 9 2015 በተለያዩ ላይቭ እና በአለምአቀፍ ዲጄዎች ሙዚቃ ጋር በማጀብ በተጨማሪም የፊፋ የእግር ኳስ ዝነኞች( ሌጀንዶችን) ደጋፊዎች የሚገናኙበትን ዕድልም በማመቻቸት በግሩም ሁኔታ እንደምታስተናግድ ታውቋል።


ፊፋ ፋን ፌስቲቫል በዓለም ላይ ታላቁ የእግርኳስ ድግስ ሲሆን በተለያዩ በተመረጡ የዓለማችን ከተሞች  የአለም ዋንጫውን ከባቢ ስሜት ለመፍጠር፣ በኳስ ዙርያ ደጋፊዎችን ወደአንድነት በማምጣት ስሜታቸውን የሚጋሩበት መልካም አጋጣሚ ሲሆን ከአለም ላይ ተሰባስበው የኳስ አፍቃርያን የማረሳ ደስታቸውን የሚጋሩበትና  በሙዚቃ በባህላዊ ዝግጅቶች ምግቦች እና መጠጦችን ጨምሮ ፊፋ የሚያዘጋጀው እውነተኛ የእግርኳስ ፌስቲቫል ነው፡፡
ከዱባይ ተጨማሪ የ2022 አለምዋንጫው ፌስቲቫል በለንደን ሜክሲኮ ሲቲ ፤ ሪዮ ዲጄኔሮ ፤ ሳኦ ፖሎ እና ሴኡል  የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል፡፡
የደጋፊዎች የእግር ኳስ ፌስቲቫል  ከተጀመረ  እንደቆየ የተለያዩ መረጃዎችን ማጣቀስ የሚቻል ቢሆንም አሁን ባለው ቅርጽ የተሞከረው ግን በ2002ቱ የኮርያ/ጃፓን አለም ዋንጫ ሲሆን ከጀርመኑ 2006 ጀምሮ በተካሄዱት 4 የፊፋ ፋን ፌስቲቫሎች ከ 40ሚልየን በላይ የእግርኳስ ወዳጆች እንደታደሙበት ሲታይ ዝግጅቱ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ ያመለክታል፡፡፡፡ በ2010ሩ የደቡብ አፍሪካ የአለም ዋንጫ ለመጀመርያ ጊዜ ከአዘጋጅ ሀገር ውጪ በሌሎች ስድስት የአለማችን ከተሞች ፌስቲቫሉ የተደረገ ሲሆን ፤ የሩስያው የ 2018 የአለም ዋንጫ ደግሞ በሩስያ ብቻ በ 11 የደጋፊዎች መሰባሰብያ ቦታ በተዘጋጀው የፋንስ ፌስቲቫል 7.7 ሚሊየን ጎብኚዎች የተሳተፉበት በመሆን በታላቅነቱ ተመዝግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *