የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ሥርጭት ለመከላከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የራይድ ትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ከአንድ ሚለየን ብር በላይ ለግሰዋል።
የራይድ ስራ አሰኪያጅ ወይዘሪት ሳምራዊት ፈቅሩ አንደገለፀችው “ዛሬ ከሰዓት 8 ሰዓት ላይ ከውድ አሽከርካሪዎቻችን ጋር በአካል ተገኝተን ላለፉት 5 ቀናት የሰበሰብነውን ሃቅ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር አስረክበናል:: በዚህ ክፉ ቀን ከኛ ችግር የወገኖቻችን ይብሳል ብላችሁ ከ 1 ብር አንስቶ እስከ 5,000 ብር ለለገሳችሁ አባላት ፈጣሪ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈላችሁ:: “

“በዚህ መዋጮ ላይ ለመሳተፍ ፈልጋችሁ በተለያየ ምክንያት መሳተፍ ሳትችሉ እድሉ ያለፋችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሳትቆጩ የቤተሰባችን አካል በመሆናችሁ በኩራት አንገታችሁን ከፍ ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን:: “
ኢትዮጽያችን የሁላችንም ድምር ናትና ጣት ሳንቀስር ከኛ የሚጠበቅብንን ማድረጋችን የእውተኛ ሰብዓዊ ዜጋ ትርጉሙ ይሄ ነው:: ስለዚህ በዚህ የጀመርነውን እርዳታ ሳናቋርጥ ካለንበት ማጥ እስክንወጣ ድረድ ለወገን ድጋፍ መሆናችንን እንድንቀጥል ለራይድ ቤተሰብ ጥሪ እናቀርባለን -” ሰትል መልክቷን አስተላልፋለች።