የመጨረሻዎቹ ሶስት የአሜሪካ ወታደራዊ የትራንስፖርት አውሮፕላኖች አፍጋኒስታንን ለቀው ወጥተዋል ።

የመጨረሻዎቹ ሶስት የአሜሪካ ወታደራዊ የትራንስፖርት አውሮፕላኖች ከሐሚድ ካርዛይ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስተው አፍጋኒስታንን ለቀው ወጥተዋል ።

ታሊባን አሜሪካ አፍጋኒስታንን ለቃ እንድትወጣ ያወጣው ቀነ ገደብ ነገ ነሐሴ 25 ከመጠናቀቁ ቀደም ብለው አሜሪካ ከአፍጋኒስታን መውጣቷን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) አረጋግጧል።

የመጨረሻው የ C-17 ግሎባስተር መጓጓዣ ዛሬ ከካቡል ከምሽቱ 3:29 ላይ የተነሳ ሲሆን የ CENTCOM ኃላፊ ጄኔራል ኬኔት ማኬንዚ “ከአፍጋኒስታን የመውጣታችን ማጠናቀቂያ” በማለት በይፋ ዛሬ ገልፀው ሆኖም አሜሪካ የፈለገውችውን ሰው ሁሉ ማስወጣት እንዳልቻለች ተናግረዋል።

“ጦርነቱ አብቅቷል። የአሜሪካ የመጨረሻ ወታደሮች ከካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ወጥተዋል ”ሲሉ የ አርቲ ሚዲያ ሙራድ ጋዝዲዬቭ ከካቡል በትዊተር ገፁ አሜሪካ በአፍጋኒስታን ላይ የነበራት ጦርነት “ 19 ዓመታት ፣ 10 ወሮች እና 25 ቀናት ”እንደፈጀ ገልፇል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *