በስራ ማቆም አድማ የተከሰሱት 9 የሲቪል አቪየሸን የበረራ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የጥፋተኛነት ፍርድ ተወሰነባቸው።
የሚከፈለን ደሞዝ አነስተኛ 000 ይጨመርልን በማለት በ2010 ነሀሴ ላይ የስራ ማቆም አድማ ያደረጉት ሰባት ወንዶች ሁለት ሴት የበረራ ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ከ16 ወራት የክስ ሂደት በኋላ ትላንት ጥር 4, 2012 ሀገርን ስጋት ላይ ጥለዋል በሚል ጥፋተኛ ተብለዋል። ነገ ልደታ ፍርድ ቤት የሚውለው ችሎት የእስር ብይን ያስተላልፍል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሰራተኞቹ ትናንት ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ቦታ ተወስደዋል።አድማ ባደረጉ ሰሞን ከአንድ ወር እስራት በኋላ ተለቀው ከስራም የተባረሩት እነዚህ ሰራተኞች በቅርቡ ተደውሎላቸው ወደ ቀድሞ ስራቸው እንደሚመለሱ ቃል ተገብቶላቸው ነበር።