በብዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደውም በመሀል ከተሞች ጭምር ለኮሮና ቫይረስ የሚያጋልጡ የሰዎች መገፋፋቶች እና የጥንቃቄ ጉድለቶች ይታያሉ ይሄ ምክንያቱ ምንድን ነው በማለት ፊደል ፖሰት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት የሆነችውን ዶክተር ባርኮት ሚልኪያስን ጠይቆ ነበር ።
እንዲህም አለች ” እወነታው ኮሮና ኢትዮጵያ ገብቷል ።ደንገጠናልም ።ነገር ግን ድንጋጤያችንን ክደን ለቫይረሱ የሚያጋልጡ ነገሮችን እየሰራን ነው ።ይሄ ቀውስ ያመጣል ።ዋጋ ያስከፍላል ። አውነታን ክደን የምናደርገው ነገር የራሳችንን የሌሎችን ሒወት ዋጋ ያስከፍላል ።ስለዚህ ቫይረሱን ፈርተን ጥንቃቄ ከወዲው ብናደርግ ከሚመጣብን ትልቅ ችግር እንድናለን ።”
ዶ/ር ባርኮት በኮሮና ቫይረስ ለሚጠቁ ሰዎችም ከወዲው የስነ ልቦና ምክር እንዲያገኙም ሰዎችን በስፋት ማሰልጠንና ማዘጋጀት ያስፈልጋል ብላለች ።