በወፍ በረር ቅኝት ባደረኩት ምልከታ በጃን ሜዳ ቅጥር ግቢና ከውጭ ባሉት አስፋልቶች 11 ታቦትን ለመሸኘት የተገኘው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመን ብዛት በግምት ከአንድ ሚልየን ቢበልጥ እንጂ አያንስም ።ግቢው ከአፍ እስከ ገደቡ ሞልቷል ።ከጠዋት 12 ሰአት ጀምሮ ፀበል ለመጠመቅና ታቦት ለመሸኘት የተገኘው ህዝብ በከተማው ያለ የእምነት ተከታይ ሁሉ ጃን ሜዳ የተገኘ ነው ሚመስለው ።በአማካኝ አንድ ታቦት በ100,000 አማኞች ታጅቦ ወደ መጣበት ቤተክርስቲያን ተመልሷል። ወጣቶች የተለያዪ ዲዛይን የሐበሻ ልብሶችን ለብሰው እየዘመሩ የእየሱስ ክርስቶስን በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥመቁ ዪሐንስ መጠመቅን ፣ጥምቀት የድህነት አንዱ ትእዛዝ መሆኑን ለማሳተማር በተለያዪ መዝሙሮች በአሉን የሚዘክር መዝሙር ዘምረዋል ።እናቶች እልልታም ታቦቱን ሸኝቶ ዳግም ወደ ቤተክርስቲያን መልሷል ።
የቤተክርቲያኗ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ጃን ሜዳ ጥምቀተ ባህር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልክት እንዳሉት በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ቃጠሎዎችና ጉዳቶች በምእመናን ላይ እምነታቸውን በነፃነት እንዳይከተሉ እያረገ ሲሆን አየደረሱ ያሉ ዛቻዎችና ማስፈራርያዎች ትልቅ የሀገሪቱ ፈተና መሆኑን መንግስት ተገንዝቦ በፀጥታ ሀይሉ በኩል ተገቢውን ከለላ ሊሰጣት ይገባል ብለዋል። ቤተክርስቲያንም እንደጥንትነቷና እንደታላቅነቷ ልትከበር ይገባል ብለዋል።