“ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች ተቃውሞን ማስነሳት እንጂ መቆጣጠር አይችሉም ” ዶ/ር ሰሚር የሱፍ



ዛሬ በአሜሪካ ኢምባሲ አስተባባሪነት መጪውን ምርጫ አስመልክቶ ለጋዜጠኞችና ፓለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ ንግግር ያደረጉት የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪው ዶ/ር ሰሚር የሱፍ እንዳሉት ” ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደጋፊዎቻቸውን አነሳስተው ተቃወሞ ማስነሳት እንደሚችሉት የተነሳውን ተቃውሞ የመመለስ ተቋዋማዊ ብቃት የላቸውም ይሄም ሀገሪቷን ግጭት ውስጥ ሊከታትይችላል “ብለዋል።
” አብዛኞቹ ተቋዋሚዎች ከብሔር ውጭ ያሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አጀንዳዎችን በማንሳት ሕዝብን የማቀራረብ ስራ በመስራት አስፈላጊ ለውጥ ማምጣት ሲችሉ አየሰሩ አይደለም ” በማለት ተችተዋል።
” በፌዴራልና በክልል መንግስት በኩል ያለው ፍትጊያ አመፅ ሲነሳ መንገስትን ቶሎ አመፁን እንዳይቆጣጠር እያረጉት ነው “ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *