በህዳሴ ግድብ “አሜሪካ ሚዛናዊ መሆን አለባት” ያለው የኮንግረሱ ሰው ስቴፈን ሆርስፎርድ ማነው?

አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ላይ ሚዛናዊ ከሆነች ኢትዮጵያ ወደ ጠረጴዛ ትመጣለች በማለት ለአሜሪካ ግምጃ ቤት ሀላፊ ስቴፈን ሙኒቺን አስተያየትና ጥያቄ ያቀረበው የ46 አመቱ ስቴፈን ሆርስፎርድ ማነው?
እናቱ ፓልሜላ በ17 አመቷ ከካረብያኗ ሀገር ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ በልጅነቷ ተሰዳ ነው የመጣችው ።በ17 አመቷ ከጋሪ ሼለተን ጋር ተወዳጅታ ሆድሰንን ላስ ቬጋስ ላይ ወለደች።ሆርስፎርድ የ19 አመት ልጅ እያለ አባቱ በጥይት ተገደለበት ።በአባቱ አሟሟት ዙርያ ሁለት መላ ምቶች አሉ ።አንደኛው ጋሪ ሼልተን በአደንዛዥ እፅ ምክንያት ወንጀል ሰርቶ ነው ሲል ሌላኛው ደግሞ በምግብ ማብሰል ተቀጥሮ ከሚሰራበት ቦታ መጋዘን አካባቢ ነው ሰዎች መጥተው የገደሉት ይላል።
ሆርስፎርድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በኢዲ ክላርክ ት/ቤት እየተማረ ፒዛ ሀት ተቀጥሮ ይሰራ ነበር ።የመመገብያ እቃዎችም ያጥብ ነበር ። 
በፓለቲካል ሳይንስ እና በኮሚኒኬሽን ከኔቫዳ ዩንቨርስቲ ዲግሪ ያገኘ ሲሆን ። 800,000 ነዋሪ ያላትን ገጠራማዋን ኔቫዳ 4ኛው ዲስትሪክትን በመወከል በአሜሪካ ምክር ቤት የኔቫዳ የመጀመርያው አፍሪካ አሜሪካ ተወካይ ነው። 
ባለፈው የፈረንጆች አመት ተመርጦ ምክር ቤት አባል የሆነው በቅርቡ ፕሬዝዳንት ትረምፕ ከዩክሬን መሳርያ እርዳታ ጋር ተያይዞ ከስልጣን ይነሱ ሲባል ሆርስፎርድ “ይነሱ” በማለት ድምፅ ሰጥቷል።” አሜሪካን ከግል ጥቅሙ ጋር የሚያያይዝ መሪ ሊመራን አይገባም ።ማንም ሰው ቢሆን ከህግ በላይ አይደለም ።ፕሬዝዳንቱም ቢሆን ” በማለት በግዜው አስተያየት መስጠቱ ይታወሳል።
ሆርስፎርድ በኢንቨስትመንት ፣በሆቴል ፣ስራ ላይ ባተኮሩ አሰልጣኝ ድርጅቶች በሀላፊነት የሰራ ሲሆን ለብዙ ወጣቶችም ስራ አስገኝቷል።
በኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ በሚገኘው የአስተማሪ ኮሌጅ ተቀጥራ ከምሰራው ዶክተር ሶንያ ሆርሰፎርድ ጋር ተጋብቶ ሶስት ልጆች አፍርቷል።የእስራኤል ጠንካራ ደጋፊ እንደሆነ የሚነገርለት ሆርስፎርድ በጦር መሳርያ አያያዝና ቁጥጥር ላይ አሜሪካ ያላትን ፓሊሲ በተደጋጋሚ ሲተች ይደመጣል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *