በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች ሬሳቸውን ከሆስፒታል አውጥቶ ውስን የሆነ ሰው ብቻ ተገኝቶ ቀብራቸው በጥንቃቄ ሰው ሳይበዛ እንዲቀበር በቂ ዝግጅት አልተደረገም ሲሉ የCOVID-19 የህክምና የሚሰጥበት የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ኪዳኔ ለፊደል ፖስት ተናገሩ።
እንደ አቶ ኪዳኔ ገለፃ በሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ማን እሬሳ ይረከባል ፣ማን ሬሳውን ያጅባል ፣ምን ያክል ሰዎች ቀብሩ ላይ መገኘት አለባቸው በሚሉት ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ሲኖርባቸው ይሄንን ስራ ለመስራት ይሄ ነው የሚባል እንቅስቃሴ አለመጀመሩን ተናግረዋል።
እንደ አቶ ኪዳኔ ገለፃ ቀብር ላይ ውስን ሰዎች እንዲገኙ ካልተደረገ ብዙ ሰው በአንድ ቦታ ላይ መገኘቱ ለቫይረሱ ለመግታት የማይመከር ነው ብለዋል።
” አስከ አሁን ሁለት ሰው ብቻ ስለሞተ ቀብሩን ለማከናወን ያን ያክል አልተቸገርን ይሆናል ።ነገስ? ብለን ግን ማሰብ አለብን ።ጤና ቢሮዎች ፣ ፖሊስ ፣የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች ፣ የሐይማኖት አባቶችና ቀብር አስፈፃሚ ድርጅቶች በዚህ ጉዳይ ላይ በቶሎ ተቀራርበው መስራት ይኖርባቸዋል ።
” አንድ ሆስፒታል አክሞ ፣የሞተውን ገንዞ ፣አንደገና ደግሞ ስለ ቀብር ፕሮግራም ተጨንቆ ብቻውን መስራት ይከብደዋል” ብለዋል።