በእስክንድር ነጋ የተመሰረተው ባልደራስ እና በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ «መኢአድ” ነገ አርብ የካቲት 27,2012 አዲስ አበባ ላይ ጋዜጠኞችን ጠርተው የውህደት ፊርማቸውን እንደሚያደርጉ ፊደል ፓስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።
ውህደታቸው በመጪው ነሀሴ ለሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ ጠንከር እና ገዘፍ ብሎ ለመፎካከር ያለመ ነው።
በመኢአድ በኩል ፕሬዚዳንቱ አቶ ማሙሸት አማረን ሲወከሉ በባልደራስ ደግሞ አቶ እስክንደር ነጋ ተወክለው ፊርማ ይፈራረማሉ።