ስምና የስራ ቦታዋ እንዲሁም ወንጀሉን መች እንደፈፀመችው ያልተነገረ ኢትዮጵያዊ ዛሬ በኵዌት በስቅላት ከተሰቀሉት ሰባት ሰዎች መሀል እንድመትገኝበት አልጀዚራ ዘግቧል።
በዛሬው እለት በስቅላቸው የተሰቀሉት እስረኞች አራት ኩዌት ፣ አንድ ፓኪስታናዊ ፣ አንድ ሶሪያዊ እና አንድ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ከሰባቱ ሁለቱ ሴቶች ናቸው።
እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 25፣ 2017 ጀምሮ ሀገሪቱን ለሁለት መቶ ተኩል የመራው የንጉሣዊው የአል-ሳባህ ቤተሰብ አባልን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ከተሰቀሉበት በኋላ የዛሬው የመጀመሪያው የሞት ቅጣት ነው።
ታዋቂው የመብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ማክሰኞ እለት ግድያዎቹ እንዲቆሙ የጠየቀ ሲሆን “የህይወት መብት ጥሰት እና የመጨረሻው ጨካኝ፣ ኢሰብአዊ እና አዋራጅ ቅጣት ነው” ኩዌት የሞት ቅጣትን “ሙሉ በሙሉ” መሰረዝ አለባት ሲልም ጠይቋል።