አምባሳደር ሪል ስቴት ነዋሪዎች በአካባቢያቸው አስተዋሽ ላጡ ቤተሰቦች የምግብ እርዳታ አድርገዋል


በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገቢያቸው ተቀዛቅዞ ችግር ላይ የወደቁ የአካባቢያቸውን ነዋሪዎች በማስታወስ አምባሳደር ሪል ስቴት ነዋሪዎች ከ250,000 ብር በላይ በማሰባሰብ ዛሬ የዘይት፣የፉርኖ ዱቄትና ማካሮኒ እርዳታ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም የሳኒታይዘር ፣ጓንት እና የአፍ ጭንበል ድጋፎችን እናደርጋለን ብለዋል ።
የነዋሪዎቹ ማህበር አቶ ገ/ መድህን በለጠ ለፊደል ፖስት አንደተናገሩት የዚህ አይነቱ ድጋፍ የፍቃድ ሳይሆን የግዴታ ነው ብለዋል።
” ታሪካችን አካፍሎ ተካፍሎ መብላት ነው ። ይሄን ነው ያደረግነው።ሁሉም ቤት እያንኳኳን ስንጠይቅ የአቅማማ ነዋሪ የለም ።።ይሄማ ግዴታችን ነው ያለው ነዋሪው ።የዚህ አይነቱ ድጋፍ ለወደፊትም ይቀጥላል። ነዋሪው በየመሰሪያ ቤቱ አንዲሁም ለመንግስትም ድጋፍ አድርጎዋል።ይሄ ደግሞ የአካባቢያችን ነዋሪ የሆኑትን ጎረቤቶቻንን ለማስታወስ ነው ።” ብለዋል።

አምባሳደር ሪል ስቴት ከ140 በላይ አባዋራዎች ይኖራሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *