ቻይና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ሰራተኞችን በመለያ ክፍል አስቀመጠችባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 12 ወደ ቤይጂንግ የበረረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤየረ ባስ አውሮፕላን ታዩያን በምትባል የቻይና ከተማ አድርጎ በሯል ።እዚያ ሲያርፍ በኮሮና የተጠረጠሩ መንገደኞች እና የበረራ ሰራተኞች ስልነበሩ ለተጨማሪ ምርመራ ለአስራ አራት ቀን በለይቶ ማቆያ እንዲኖሩ መደረጉን ከፖይለቶቹ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።
ፓይለቶቹን ጨምሮ መለያ ክፍል ውስጥ የተቀመጡት የበረራ አስተናጋጆቹ ቁጥር 25 እንደሚሆንና የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።

ፊደል ፖስት እንደተረዳወ ፓይለቶቹ ባዶውን አውሮፕላን ከታዩያን ወደ ቤይጂንግ ይዘው ሄደዋል ።ቀጠሎ ግን አብራሪዎችን እዚያው ታዩያን በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ተደርገዋል።

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ፊደል ፖስት የአየር መንገድ ህዝብ ግኑኝነት ክፍሉን ቢጠይቅም መልስ ማግኘት አልቻለም ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *