“ተማሪዎቹን ያገተው አይታወቅም ።1.2 ሚልየን ወጣት ስራ አስይዘናል።የህዳሴን ግድብ ፊርማ ስምምነትን አዘግይችዋለው ” ጠ/ሚ አብይዛሬ ጥር 25 ,2012 በህዝብ ተወካዮች ፊት ቀርበው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከቤተሰባቸው እስከአሁን ያልተገናኙትና በደምቢዶሎው ዪንቨርስቲ ይማሩ የነበሩና እገታ ስለደረሰባቸው ተማሪዎች ጉዳይ በሰጡት ምላሽ ” የሞተ ወይንም የተጎዳ ተማሪ የለም። ልክ አንደ ናይጀርያው ቦኮ ሀራም ለፈፀመው ወንጀል ሀላፊነቱን በሚወስድ ቡድን አይደለም የታገቱት ።ማን እንዳገታቸው? አይታወቅም ይሄም ስራችን ኣዳጋች አድርጎታል ።ሆኖም ግን መንግስት በሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈርያት ከሚል እና በም/ትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ በኩል ኮሚቴ አዋቅሮ ለችግሩ አልባት ለመስጠት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስታቸው በውስጥ ጠላቶች ፈተና እንደገጠመውም አስረድተዋል።
” ተቋሞቻችን በሽግግር ላይ ስላሉ በሁለት እግራቸው አልቆሙም ።የውስጥ ጠላቶች ቢከቡንም ወደፊት ከመጓዝ አልቦዘንም ። አልሻባብ ሀገራችን ላይ ብዙ ጊዜ ጥቃት ለማድረስ ቢሞክረም አክሽፈናዋል ።ጥቃቱ ቢደርስ ትልቅ ፈተና ውስጥ እንወድቅ ነበር ።የከሸፈ እቅዳቸውን ለህዝብ ወደፊት የምንናገር ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስታቸው በሰባት ወር 12 ቢልየን ብር ገቢ አንዳስገባ እና 1.2ሜልየን ወጣቶች የስራ እድል እንደተፈጠረ ተናግረዋል።
” ለ3 ሚልየን ወጣት በአመቱ ውስጥ የስራ እድል እንፈጥራለን ብለን 1.2ሚልየን ወጣት ስራ አስገኝተናል ቀሪዎችንም ለማስያዝ እንሰራለን። አፋርና ሱማሌ ላይ 20,000 ሄክታር ለስንዴ የሚሆን መሬት በመስኖ አልምተናል ።ምርትም ለወደፊትም እናገኝበታለን ። የበረሀ አንበጣ ትልቅ ፈተና ሆኖብናል ።ግብርና ሚኒስቴር የበለጠ አደጋ እንዳይከተል ኮሚቴ አዋቅሮ እየሰራ ነው ።የህዳሴ ግድብ በሶስት አመት ያልቃል ።ሀይል ሲያመነጭም በአመት አንድ ቢልየን ዶላር ያስገኝልናል። በግድቡ ዙርያ በአሜሪካና በአለም ባንክ የነበረው አደራዳሪነት መልካም ነበር። ነገር ግን ለፊርማ የመጣልኝን ዶክመንትን በደንብ ለማጤን ስለፈለግኩ ግዜ ስጡኝ ብዬ አራዝሜዋለው።
” ግድቡን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ መሪ ስራውን እና ድርድሩን አስጀምረዋል ።አሁን ግድቡን አትስሩ ሳይሆን እኛን አትጉዱን የሚል ነው ክርክሩ ።እኛም ግብፅን ብዙም በማይጎዳ እኛንም ጥቅማችንን በማያሳጣ ሁኔታ ስምምነት እናካሄካደለን ብለን እንጠብቃለን ” ብለዋል።
የትግራይ ክልል ተወላጆች ያለ አግባብ ከስልጣን እየተነሱ ነው ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ ” ብዙ ሚኒስቴር ዴኤታዎች ከትግራይ አሉ ።ይሄ ተራ አሉባልታ ነው ብለዋል።”
በወለጋ ስላለው ውጊያ ሲያብራሩ ” ማንም እንደሚያውቀው” ኑ “በሰላም ለፓለቲካዊ ለስልጣን ተወዳደሩ ፣ተወያዩ ፣ተከራከሩ ብለን ሜዳውን ከፍተናል። አንዳንዱ ይሄ መንገድ ያለመደው ስለሆነ በህገወጥ መንገድ ስልጣን ለመያዝ ይሞክራል ።ይሄ አግባብ ስላልሆነ አንደመንግስት እርምጃ አየወሰድን ነው ” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *