“ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል አልታገቱም ዛሬ ቀን 10 ሰአት ላይ አውርቻቸዋለው ” አባ ቲቶ አዳነ



የጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ባልታወቁ ሀይሎች ታግተዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚድያ ስለተሰራጨው ዜና ለማጣራት ፊደል ፖስት የጋምቤላና የደቡብብ አህጉረ ስብከት ምክትል ስራ አስኪያጅ አባ ቲቶ አዳነ ስራ አስኪያጅ ጠይቆ እንደተራዳው ሊቀ ጳጳሱ በስራ ላይ እንደሆኑ ተነግሮታል ።
” እሳቸው የቅድስት አርሴማን ገዳም እያቀኑ ነው ።አስር ሰአት ላይ በስልክ ተገናኝተን አውርቻቸዋለው ደህ ነኝ የየዝኩትን ስራ ስጨርስ እመጣለው ብለዋል ።ሌላው የሚወራው የሀሰት ወሬ ነው ።ቤተክርስቲያናችን ለመረበሽ በማሰብ ” ሲሉ አባ ቲቶ መልሰዋል።
” የሀሰት ወሬ ሲያስጨንቀን የፀጥታ አካላት ጋር እና የመንግስት ሀላፊዎቹም ጋር ደውለን ነበር ።ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ብለውናል ሲሉ ነግረውናል “ሲሉ አስረድተዋል

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ ዶምቢዶሎ ላይ ገዳም የማቋቋሙን ሒደት ለመከታተል፣ ከአዲስ አበባ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ቄለም ወለጋ የተጓዙት፣ ከአንድ ሳምንት በፊት፣ የካቲት 28 ቀን ሲሆን በስፍራው ከተሾሙ ደግሞ ሶስት አመት ይሞላቸዋ።ል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *