“ቤተክርስቲያን ልትፈርስ ነው ብለው ቄሶች ጥሪ አቀረቡ።ህዝቡም ወጣ ።በነበረውም ተኩስ ሰዎች ሞቱ።” ነዋሪዎች


ወንድሟ በጥይት ተመቶ አቤት ሆስፒታል የተኛባት ቅድስት ሀይሉ ስለነበረው ክስተት እንዲህ ስትል ለፊደል ፓስት ተናግራለች ።” ይሄ 22 ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ጀርባ የሚገኘው ቦታ ለረጅም አመታት ታጥሮ የቆየ ነው ። ምን አልባት 17 አመት በላይ ።ለቤተክርስቲያንም አገልግሎት እንዲሆነ ከተጠየቀ ቆይቷል ።ባለፈው ቅዳሜ የአርሴማ ማርያም እና የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ገብቶበት አገልግሎት ጀመረ ።ፓሊሶች ትናንት እኩለ ለሊት ካለፈ በኋላ ቦታውን ለማፍረስ መጡ ።በሁኔታው የተደናገጡት ቄሶች በማይክራፎን ምእመኑን የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ ። የአካባቢውም ህዝብም ግልብጥ ብሎ ወጣ።አስለቃስ ጭስ ተተኮሰ ፣ተከታታት ተኩሶች ነበሩ ።የፓሊስም መኪና ተቃጠለ ።ጩኸት ለቅሶ ይሰማ ነበር።የፌዴራል ፓሊስም ብዛት ቦታዉን የተወረረ ከተማ አስመሰለው።ህልም እንጂ እውን አይመስልም። ። ሁለት ሰዎች ሞቱ ።የእኔን ወንድም የግራ እጅኑ ተመታ ።ወደ 15 ሰውም ቆሰለ ። አምቡላንስ ተጎጂዎችን ኮርያ እና አቤት ሆስፒታል እይሰዱ ነበር ።ሲነጋ የአካባቢው ሱቆች ተዘግተው ባለቤቶችም ስለተፈጠረው ነገር ግራ ገብቷቸው ስለሞቱት ሰለቆሰሉት ሰዎች በጣም አዝነው እያወሩ ነበር። ፓሊሶች ማፍረስ ከፈለጉ ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጋር ተማክረው መፍትሄ ማበጀት ይችሉ ነበር ።ለሊት እንደሌባ መጥተው ማፍረሳቸው የሰው ሒወት አሳጥቶናል ።”
የአካባቢው ፓሊስ መምሪያ በሰጠው ምላሽ ህገወጥ ግንባታዋን በቀን ማፍረስ ሁከትን ያባብሳል ተብሎ ነው በማታ ለማፍረስ ታቅዶ የነበረው የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ቦታውን እንዲፈርስ ቢጠይቅም ሰሚ አካል አለማግኘቱን ተናግረዋል።
የከተማው ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ትናንት ማታ ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚድያ ገፃቸው ባሰፈሩት አስተያየት እንዲህ ብለዋል።

“ከየትኛውም ጊዜ በተለየ ከኃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርበን እየሰራን እንገኛለን።ከስራችን ጅማሬ አንስቶ የደከምንበት የሃይማኖት ተቋማት ጥያቄዎች ምክንያት አንድም የሰው ሕይወት ይጠፋል ብለን አስበን አናውቅም።በተለይም የይዞታ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ረጅም ርቀት ሄደን ጥያቄዎችን ስንመልስ ቆይተናል።ይሁን እንጂ በመንግሥት እና በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ጥቂት አጥፊዎች ምክንያት በከተማችን ይሆናል ያላልነው ፤እንዳይሆንም የለፋንበት ድርጊት ተፈጽሟል።

“ከተማችንን በመለወጥ ሂደት ውስጥ ህይወታቸው ይለወጣል ብዬ ከማስብላቸው ወጣቶች ሁለቱን አጥተናል።እነዚህን ወጣቶች ለማጣት ያበቁንን በየትኛውም ወገን ያሉ የጥፋቱ አካላትን በሕግ እንዲጠየቁ እናደርጋለን።በጥፋቱ ወንድሞቻችንን አጥተናል። ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ። እጅግ አዝኛለሁ።” በማለት ፅፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *