ባለፉት 6 ወራት ብቻ 16 ዝሆኖች ተገድለዋ

በ6 ወራት ብቻ 16 ዝሆኖች በሕገወጥ አዳኞች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው የዱር እንስሳት መካከል ዝሆን አንዱ ነው፡፡ በዚህ መልኩ የሚካሄድ ሕገወጥ ተግባርን ማስቆም ካልተቻለ በኢትዮጵያ ዝሆን የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን አስታውቀዋል፡፡ 

በኢትዮጵያ ከ1800 የማይበልጡ ዝሆኖች እንዳሉ በዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የዱር እንስሳት ሕግ ማስከበር ዳይሬክተር ዳንኤል አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ቀጥተኛ ከሆነ ህገወጥ የዝሆን አደን በተጨማሪ በጥበቃ ስፍራዎች ላይ የሚደረጉ የሕገወጥ ሰፈራዎች፣ ሕገወጥ አደን፣ ደን ምንጣሮ እንዲሁም እርሻ ለዱር እንስሳቱ ዛሬም ድረስ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ነው የተናገሩት፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ብቻ በኦሞ እና ማጎ ብሔራው ፓርኮች ስድስት ዝሆኖች መገደላቸውን እና ጥርሳቸውም መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *