በ 9919 የስልክ ጥሪ የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት ፈላጊዎች አገልግሎት የሚያገኙበት ራይት ራይድ የሚባል የሜትር ታክሲ ዛሬ አገልሎቱን በይፋ ጀምሯል።
በእይታ ቢዝነስ ሶሊዩሽን ሃ/የተ/የግ/ማ አቅራቢነት በዛሬው እለት በይፋ በአዲስ አበባ ስራ የጀመረው ራይት ራይድ (RR) ከ4000 በላይ አሽከርካሪዎችን በአባልነት መያዙ ተነግሯል ።
የእይታ ቢዝነስ ሶሉሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ሁሴን እንደተናገሩት አገልግሎቱን ተጠቃሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ራይት ራይድ የተሰኘውን የሞባይል መተግበሪያ ከፕሌይ ስቶር በማውረድ ወይም በ 9919 ላይ በመደወል አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።
የሞባይል መተግበሪያው ትእዛዝ ከመቀበል ባለፈ የአሽከርካሪውን ደህንነት የሚያሳውቅ የአስቸኳይ ጊዜ የአደጋ ጥሪ ገጽታ እንዳለው ተገልጿል ።
በ5 በመቶ የኮሚሽን ክፍያ አገልግሎት እንደሚሰጥ ያስታወቀው ድርጅቱ ለቀጣዮቹ ሶስት ወራት ያለ ኮሚሽን ክፍያ እንደሚሰራ ገልጿል ።
የመነሻ ዋጋው 50 ብር ሲሆን በኪ.ሜ 12 ብር እንደሚያስከፍል ታውቋል።
እንዲሁም ራይት ራይድን የሚጠቀሙ አሽከርራካሪዎች የመኪና እጥበትና አገልግሎትን የመኪና ዘይትን ግዢን በተወሰነ ቅናሽ ያገኛሉ ተብሏል።