የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በቤተመንግስታቸው ኋይት ሀውስ ሆነው ባህሬን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዛሬ በይፋ እስራኤልን እንደሀገር የተቀበሉበትን ፊርማ ሲፈረሙ ታዛቢ ሆነዋል ።
” ከብዙ አስርት አመታት ግጭትና ክፍፍል ዛሬ አዲስ የሰላም መንገድ ጀምረናል ሌሎች የቀጠናው ሀገራትም ተመሳሳይ ፊርማ ያኖራል ። እሱም በጣም ቅርብ ነው ” በማለት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የተናገሩ ሲሆን አምስት ተጨማሪ ሀገራት ከእስራኤል ጋር ለመስራት ተቃርበዋል ቢሉም ስማቸውን ግን አልጠቀሱም።
የእስራኤሉ ጠ/ ሚ ቢንጃሚን ኔታንያሁ ስምምነቱን “የአብርሀም ልጆችን ያቀራረበ ” በማለት አውድሰው ባህሬን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለእስራኤል እውቅነሰ ስለሰጡ አመስግነው ሌሎች አረበረ ሀገራትም ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርጉ ተስፋ አድርገዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስት ሼኪ አብዱላሂ ቢን ዘይድ በበኩላቸው ” ዛሬ አዲስ ጅማሮ መስክረናል ይሄም ጅማሬ ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ያመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። ሰላም ደግሞ ትጋት እና ወኔ ይፈልጋል ” ብለዋል።
ባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱለሰቲፍ ቢን ራሺድ አል ዛይኒ ደግሞ ” ለረጅም ግዜ መካከለኛው ምስራቅ የቅጭትና የጥርጣሬ ቦታ ነው ዛሬ ግን በዚህ ስምምነት ይሄን መቀየር እንደሚቻል አምኛለው ” ብለዋል።
ባህሬን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ግብፅና ዮርዳኖስን ተቀላቅለዋል ።
የንግድ እና የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን ከእስራኤል ጋር ሀ ብለው በመጀመር አጠናክረው ይገፉበታል ተብሎ ይጠበቃል ።ይሄ ጉዳይ ከፍልስጤም ፣ከኢራን እና ከቱርክ ጠንካራ ተቃውሞ ቢገጥመውም።